የ19 አመቱ አትሌት መሀመድ አማን | ባህል | DW | 10.05.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የ19 አመቱ አትሌት መሀመድ አማን

መሀመድ በአጭር ርቀት የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ በመሮጥ የራሱንና የኢትዮጵያን ስም በማስጠራት ላይ የሚገኝ ወጣት አትሌት ነው። በዛሬው ዕለትም ዲያመንድ ሊግ በመባል በሚታወቀው የምርጥ አትሌሎች የሩጫ ውድድር በ 800 ሜትር ለመካፈል፤ ቀጣር መዲያ ዶሀ ይገኛል።

Läufer in Äthiopien geschickt von Klaudia Pape DW-Radio Redakteurin Zeitgeschehen Bilder von Alexander Göbel Cell: +49-(0)-173-734-4060 Home: +49-(0)-228-249-6946 Schumannstr.40 D-53113 Bonn alexgoebel@yahoo.com

የ19 አመቱ መሀመድ አማን ተወልዶ ያደገው በአርሲ ፤አሰላ ከተማ ነው። እሱ እንደሚለው የሩጫውን አለም እንደቀልድ ነው የተቀላቀለው። መሀመድ ዛሬ ሌሎች አይናቸውን ተክለው ሲሮጥ የሚከታተሉት አትሌት ለመሆን በቅቷል። መሀመድ እንደ በርካታ የኢትዮጵያ አትሌቶች ትውልዱ አርሲ አካባቢ ነው። ለብዙ አትሌቶች ስኬት የሆነው ሚስጥሩ ተግቶ መስራት ነው ይላል።

ወጣቱ በወጣቶች የኦሎሞኒክስ አትሌቲክስ ውድድር፣ በአለም ወጣቶች ሻምፒዎና ውድድሮች እና ሌሎችም የመካከፈል እና የማሸነፍ እድል ገጥሞታል። ዛሬ ደግሞ (ግንቦት 2፤ 2005) ዶሀ ላይ ጎልደን ሊግን በተካው ድያመንድ ሊግ በመባል በሚታወቀው እና እኢአ ከ2010 ጀምሮ በሚካሄደው ውድድር ይሳተፋል።

መሀመድ ስለ የአትሌቲክስ ህይወቱ ከዶይቸ ቬለ ጋ ያደርገውን ቆይታ የድምፅ ዘገባውን በመጫን መስማት ይችላሉ።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic