የ SMS ቁጥጥር በኬንያ | አፍሪቃ | DW | 29.10.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የ SMS ቁጥጥር በኬንያ

በመጪው መጋቢት ወር በኬንያ በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ፖለቲከኞች እና ፓርቲዎች ለህዝብ የሚልኩትም አጭር የጹሁፍ መልዕክት አስቀድሞመው ማሳወቅ ይኖርባቸዋል። ይህ የSMS ቁጥጥር የኬንያ ምርጫን በርግጥ ከአመፅ ሊያድን ይችል ይሆን?

--- für die Redaktion Portugiesisch für Afrika --- Eine junge und moderne südafrikanische Frau mit ihrem Mobiltelefon, aufgenommen am Donnerstag (20.11.2008) in der südafrikanischen Hauptstadt Pretoria. Foto: Gero Breloer +++(c) dpa - Report+++

Symbolbild SMS Afrika Handy

እኢአ 2007 ዓም በኬንያ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በተለያዩ የፓርቲ አባላት እና ጎሳዎች መካከል በተነሳ አመፅ ከ 1000 በላይ ሰዎች ህይወት መጥፋቱ እና በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎች መሰደዳቸው የሚታወስ ነው። በመጪው መጋቢት ወር በኬንያ ቀጣይ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ይካሄዳል። በአሁኑ ምርጫም ያለፈው አይነት አመፅ ተነስቶ ግድያ እንዳይፈፀም በሀገሪቱ  ትልቅ ስጋት አለ።  አንዳንድ ተንታኞች እንደሚሉት ባለፈው ምርጫ  ብጥብጡን ያፋፋመው ጥላቻ የተሞላ አጫጭር የፁሁፍ መልዕክት ነው። ይህን ለማስቀረትም ቅድመ ምርመራ እንዲካሄድ መወሰኑን የኬንያ የመገናኛ ብዙኻን ገልፀዋል።

A Masai woman casts her vote at a polling station in Ngong Town, some 40 kilometers (about 25 miles) from Nairobi, Kenya Wednesday, Aug. 4 2010. Long lines of voters formed before sunrise in the Kenyan capital early Wednesday, as voters cast ballots on a new constitution that would reduce the powers of the presidency and give citizens a bill of rights. (AP Photo/Sayyid Azim)

የድምፅ አሰጣጥ በኬንያ

የኬንያ የመገናኛ ዘዴዎች ጉዳይ ምክትል ዳሬክተር ክርስቶፈር  ከሚ አዲሱ የSMS ቁጥጥር መመሪያ የሚኖረውን አስተዋፅዎ ያብራራሉ።

« የመመሪያዎቹ አላማ በመሰረቱ አንዳንድ ሰዎች በተለይም ፖለቲከኞች የምርጫ ዘመቻቸውን በሚያካሂዱበት ወቅት በሞባይል የሚሰዱት መልዕክት ይዘት የሃገሪቱን ህገ መንግስቱን የማይፃረሩ እንደሆኑ ሰዎች ያለ ፍርሃት ህጉን የሚጥሱበትን ሁኔታ ለመቀነስ ነው»

የምርጫ ዘመቻ መልዕክቶችን የሚቆጣጠረው የመገናኛ ዘዴዎች ጉዳይ የሆነ አንድ የመንግስት መስሪያ ቤት ነው። ፖለቲከኞች ለህዝቡ ለመላክ የሚፈልጉትን መልዕክት 48 ሰዓት አስቀድመው እንዲያስረክቡ አዲሱ መመሪያ ያሳስባል። የሀገሪቱ ዕለታዊ ጋዜጣ « DAILY NATION» እንዳስታወቀው መልዕክቱ በእንግሊዘኛ እና በሱሀሊኛ ቋንቋ ብቻ መሆን አለበት ። መልዕክቱ የሚደርሳቸው ሰዎች ደግሞ አስቀድመው ይህንን አገልግሎት የተኮናተሩ ናቸው።  ህዝቡ ይህንን የመልዕክት ይዘት ቅድመ ቁጥጥር እንዴት ተቀበለው? አሁንም ክርስቶፈር  ከሚ « በአጠቃላይ ጥሩ ምላሽ ነው የነበረው። በዚህ መመሪያ ላይ አስተያየት የሰጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ ይህንን አሰራር በቀና ተቀብለውታል። ምክንያቱም ሁሉም ኬንያዊያን ምርጫውን ተከትሎ በ2007 እና በ2008 የተከሰተውን በድጋሚ ማየት አይፈልጉም።»

Luo supporters of Orange Democratic Movement of opposition leader Raila Odinda burn posters of Mwai Kibaki, President of Kenya, in the Kibera slums on the outskirts of Nairobi, Saturday, Dec. 29, 2007. Thousands of people waved machetes and shouted tribal epithets Saturday in one of Africa's largest slums as tensions flared over delays in results from Kenya's presidential election, witnesses said. Millionaire opposition candidate Raila Odinga appeared to be leading the closest race in Kenya's history, but only partial and unofficial tallies have been released from Thursday's vote. Early Saturday, some results were showing President Mwai Kibaki narrowing the gap. (AP Photo/Khalil Senosi)

ከአምስት አመት በፊት ምርጫውን አስከትሎ የተነሳው አመፅ እና አለመረጋጋት

ፖሊስ ህግ የሚጥሱትን በቁጥጥር ስር ለማዋል አስፈላጊውን መሳሪያ እየቀረበለት መሆኑን ክርስቶፈር  ከሚ ከዶይቸ ቬለ ገልፀዋል። አዲሱ መመሪያ በርግጥ የምርጫ ዘመቻው ከቁጥጥር ውጪ እንዳይሆን ሲባል የታሰበ ነው፤ ወይንስ ሀሳብን በነፃ የመግለፁን መብት መመሪያው ይፃረራል? ክርስቶፈር  ከሚ፤ « መመሪያው የታቀደበት ዋና አላማ በምርጫ ዘመቻው ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ ሰዎች አላማቸውን ሳያሳንስ የሚተገብሩበት መንገድ ይሆናል። የህዝቡን ወዳጅነት እና ደህንነት እንደተጠበቀ ሆኖ።»

ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የቀረቡት ፤ ራይላ ኦዲንጋ፣ ካሎንዞ ሙስዮካ፣ ኡሁሩ ኩንያታ እና ዊልያም ሩቶ ሁሉም ለደጋፊዎቻቸው ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ በአጭር የፁሁፍ መልዕክት ወይንም SMS ተደራሽ ያደርጋሉ።  በርግጥ መመሪያው ለምርጫ ዘመቻው የነበረውን ሚና ግን ከምርጫው በኋላ የምናየው ይሆናል።

ልደት አበበ

ሒሩት መለሰ