የ ICC እና የአፍሪቃ መንግሥታት ዉዝግብ | አፍሪቃ | DW | 25.11.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የ ICC እና የአፍሪቃ መንግሥታት ዉዝግብ

እስካሁን ድረስ ብሩንዲ፤ ጋምቢያ እና ደቡብ አፍሪቃ ፍርድ ቤቱ አፍሪቃዉያንን መጨቆኛ መሳሪያ ሆኗል በማለት ከአባልነት ሲወጡ፤ ሌሎችም ለመዉጣት እያስጠነቀቁ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:51
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:51 ደቂቃ

ICC እና የአፍሪቃ መንግሥታት

ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት (ICC) ከአፍሪቃ መንግስታት የሚሰነዘርበት ቅሬታና ወቀሳ እንደቀጠለ ነዉ። ዘ-ሔግ ኔዘርላንድስ የሚያስችለዉ ፍርድ ቤት ሥራዉን የጀመረዉ እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር በ2002 ነበር።የፍርድ ቤቱን መመሥረቻ ሰነድ 124 ሐገራት ቢፈርሙም በፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ዉስጥ ድምፅን በድምፅ የመሻር ሥልጣን ያላቸዉ ዩናይትድ ስቴትስ፤ ሩሲያና ቻይና ግን አልፈረሙም። እስካሁን ድረስ ብሩንዲ፤ ጋምቢያ እና ደቡብ አፍሪቃ ፍርድ ቤቱ አፍሪቃዉያንን መጨቆኛ መሳሪያ ሆኗል በማለት ከአባልነት ሲወጡ፤ ሌሎችም ለመዉጣት እያስጠነቀቁ ነዉ። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic