1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ “ፈላታ” ማህበረሰብ በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ ያሳደሩት ተጽዕኖ

ዓርብ፣ ሰኔ 28 2016

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ከሱዳን አዋሳኝ አካባቢዎች ያሉ በግብርና ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሀብቶች በተለምዶ “ፈላታ” እየተባሉ በሚጠሩ የናይጀሪያ ተዘዋዋሪ አርብቶ አደሮች ተፅዕኖ እየደረሰባቸው እንደሆነ ባለሀብቶቹ ተናገሩ ። የዞኑ አስተዳደር በበኩሉ ችግሩ ቢኖርም ተፅዕኖው ቀላል ነው ብሏል፡፡

https://p.dw.com/p/4hvKS
Äthiopien | Region um Quara und Shinfa
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

በፈላታዋዎች የሚደርስ ተጽዕኖ የክልሉን የግብርና ኢንቨትመንት እየጎዳ ነው ፤ ባለሃብቶች

የ “ፈላታዎች” ተጥዕኖ በግብርና ኢንቨስትመንት

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ከሱዳን አዋሳኝ አካባቢዎች ያሉ በግብርና  ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሀብቶች በተለምዶ “ፈላታ” እየተባሉ በሚጠሩ የናጀሪያ ዘላን ተንቀሳቃስ አርብቶ አደሮች ተፅዕኖ እየደረሰባቸው እንደሆነ ባለሀብቶቹ ተናገሩ፣እንደአስተያተ ሰጪዎቹ፣ ፈላታዎች በመሳሪያ በመታገዝ ጭምር የእርሻ ማሳዎችን ይነጥቋቸዋል፤ የዞኑ አስተዳደር በበኩሉ ችግሩ ቢኖርም ተፅዕኖው ቀላል ነው ብሏል፡፡

በተለምዶ  በኢትዮጵያውያን ዘንድ “ፈላታ” እየተባሉ የሚጠሩና መሰረታቸው ናጀሪያ እንደሆነ የሚታመኑ ተንቀሳቃሽ ከብት አርቢዎች እንስሳቶቻቸውን ለመመገብ ኢትዮጵያን ጨምሮ ወተለያዩ የአፍሪካ አገሮች  ቆላማ አካባቢዎች ይዘዋወራሉ፡፡

በምዕራብ ጎንደር ዞን በተለይም መተማና ቋራ ከሱዳን በሚያዋስኑ ቦታዎች ሰፍረው እንደሚገኙ የዞኑ አስተዳደር አመልክቷል፡፡

ዝርፊያ እና ግድያ በአማራ ክልል

ታዲያ እነኚህ አገር አቋራጭ አርብቶ አደሮች በአካባቢው በተሰማሩ የግብርና ባለሀብቶች ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠሩ እንደሆነ ነው ባለሀብቶች የሚናገሩት፡፡

“... ከናይጀሪ የመጡና ከሱዳን ተጠግተው የሚኖሩ ፈላታ የሚባሉ ከብት አርቢዎች አሉ፣ ከእነርሱ ጋር በተያያዘ ሁሌም፣ ንብረት የምንሸክፈው በጦርነት ነው፣ መንግስት መሬቱን ለኢንቨስትመንት በሊዝ ቢሰጠንም  ፈላታዎች እንደፈለጉ ከብታቸውን በማሳው ላይ ይለቅቃሉ፣ ሲፈልጉ ራሳቸውም ገብተው ንብረት ቃትላሉ፣ ዘርፈው ይሄዳሉ፣ በዚህ ምክንያት አምናና ካች አምና እንደዛ እደረጉን ብንቆይም ዘንድሮ ደግሞ በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ማምረት አልቻልንም፡፡”

በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ አካባቢ
እነኚሁ ተዘዋዋሪ አርብቶ አደሮች የጦር መሳሪያ የታጠቁ መሆናቸውን የነገሩን ሌላው አስተያየት ሰጪ ባለሀብት፣ ሰዎቹ በፈጠሩባቸው  ጫና ከ800 ሄክታር ማሳ በላይ ለቅቀው ለመውጣት መገደዳቸውን አመልክተዋል፡፡ምስል DW/Alemenew Mekonnen

እነኚሁ ተዘዋዋሪ አርብቶ አደሮች የጦር መሳሪያ የታጠቁ መሆናቸውን የነገሩን ሌላው አስተያየት ሰጪ ባለሀብት፣ ሰዎቹ በፈጠሩባቸው  ጫና ከ800 ሄክታር ማሳ በላይ ለቅቀው ለመውጣት መገደዳቸውን አመልክተዋል፡፡

የአማራ ክልል ተፈናቃዮች አቤቱታ

“... ወደ 800 ሄክታር ለእርሻ የፀዳውን ለቅቄ ነው አሁን ገባ ብዬ 300 እና 400 ሄክታር እለማሁ ለሁት የበፊቱን ከለቀቅነ ቆይተናል፣ ምክንቱም የፈላታውን ከብት መቆጣጠር አልቻልንም፣ አርሰን ብናለማም ከብቶቻቸውን አምጥተው ስበሉታል፣ ጉዳዩ ከአቅማችን በላይ ሆነ፣ ሥራ እየሰራን ኤደለም ፣ የጦር መሳሪያ በደንብ የታጠቁ ናቸው፡፡”

መንግስት የማያውቃቸው አዛዥ የሌላቸውና የኢትዮጵያውያንን ግብርና ኢንቨስትመንት እየጎዱ መሆኑን ሶስተኛው አስተያየት ሰጪ ገልጠዋል፡፡

በአማራ ክልል የምዕራብ ጎንደር ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ቢሆነኝ ችግሩ በአንዳንድ አካባቢዎች መኖሩን ጠቁመው ሆኖም ፈላታዎች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች ኃይሎችም የግብርና ኢንቨስትመንቱን እንቅስቃሴ እያወኩት እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

የአማራ ክልል ባለሥልጣናት የሰላም ጥሪና የድርድር ሃሳቦቻቸው

“የመተማን ወረዳ ብቻ ብናይ ቱመት ቀጠና በርትራድ፣ በዲብሎና ጅብሎ ስኳርና በሌሎችም አካባቢዎች በህገወጦች ማንገራገር ምክንያት ትንሽ ከእርሻው ላይ እንቅፋት እንደገጠማቸው አርሶ አደሮችና ባለሀብቶች ይነግሩናል፣ የፈላታ ቡድኑ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ታጣቂዎችም ተመሳሳ ችግር ፈጥራሉ፣ ችግሮች እንዲፈቱ ባለው የፀጥታ ኃይል ጋር በመተባበር ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡” ብለዋል፡፡

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የውስጥ ችግሮች መፈታት እንዳለባቸው ጠቁመው ያን ለማድረግም ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል፡፡

ተጨማሪ አስተያየት ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ለማካተት ብንሞክርም የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ስልክ አይነሳም፡፡

የመንገድ መዘጋት በምዕራብና በምስራቅ ጎጃም ዞኖች

ፈላታዎች ወይም የናይጀሪያ ዘላኖች ለእንስሶቻቸው ምግብ ፍለጋ በሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳቶቻቸውን ይዘው በብዙ የአፍሪካ አገሮች ቆላማ ቦታዎች እየተዘዋወሩ እንደሚኖሩ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ዓለምነው መኮንን

ታምራት ዲንሳ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር