የ ዮ ኤስ ምክትል ፕሬዜደንት ጆ ባይድንና የእስራኤል ጉዞአቸው | ዓለም | DW | 09.03.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የ ዮ ኤስ ምክትል ፕሬዜደንት ጆ ባይድንና የእስራኤል ጉዞአቸው

ትናንት እስራኤል የገቡት ባይድን አካባቢዉን ለአምስት ቀናት ይጎበኛሉ። በዚህ ቆይታቸዉ ከኢስራኤል፣ በተጨማሪ ከፍልስጤም ራስ ገዝ፣ ከግብፅና ከዮርዳኖስ መሪዎች ጋር ይነጋገራሉ ።

default

ባይደን እና ኔታንያሁ

የ ዮ ኤስ ምክትል ፕሬዜደንት ጆ ባይድንና የእስራኤል ጉዞአቸው

በመካከለኛው ምስራቅ ባሉ አገሮች ላይ ለተዘረጋው የሰላም ማስፈስ አላማን ለማሳካት የዮ ኤስ ፕሬዜደንት ባራክ ኦባማ ምክትል ፕሬዜደንት ጆ ባይድንን ወደ እስራኤል ልከዋል። ትናንት እስራኤል የገቡት ባይድን አካባቢዉን ለአምስት ቀናት ይጎበኛሉ። በዚህ ቆይታቸዉ ከኢስራኤል፣ በተጨማሪ ከፍልስጤም ራስ ገዝ፣ ከግብፅና ከዮርዳኖስ መሪዎች ጋር ይነጋገራሉ ።

ፕሬዜደንት ባራክ ኦባማ ስልጣን ከያዙ ወዲህ አንድ ከፍተኛ የ ዩ ኤስ አሜሪካ ባለስልጣን አካባቢውን ሲጎነኝ ምክትል ፕሬዜደንት ጆ ባይድን የመጀመሪያው ናቸው። የባይድን ጉብኝት የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም ድርድር ባለበት እንዳይቀር የኦባማ አስተዳደር የሚሻ መሆኑን አመልካች ነው። ባይድን ዛሬ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እና ከሌሎችም የእስራኤል ባለስልጣናት ጋር ተወያይተዋል። ከውይይቱም በኋላ የእስራኤልን ደህንነት ለማክበር ዮ ኤስ አሜሪካ ከጎኗ እንደምትቆም ባይድን ቃል ገብተዋል። በተለይም በኢራን የኑኩሌር መርሀ ግብር የተነሳ የኢስራኤል መንግስት አደጋ እንዳይደርስባት አሜሪካ አበክራ ትጥራለች፤ እንደ ባይድን መግለጫ

OTON ባይድን

በመካከለኛው ምስራቅ መልካም ለውጥ የሚኖረው፤ ማንም ሰው እንደሚያውቀው

በዮ ኤስ አሜሪካና በኢስራኤል መካከል ምንም አይነት ክፍተት ሳይኖር ነው። የኢስራኤልን ፀጥታ በተመለከተ ከዮ ኤስ አምሪካና ኢስራኤል መካከል ምንም አይነት ክፍተት የለም። በዚህና በሌሎችም ምክንያቶች፤ የኢራን የኒኩሌር መርሀ ግብር በጥብቅ መከታተል ከመስተዳደራችን ቅድሚያ ትኩረቶች አንዱ ነው። ኢራን የኒኩሌር ጦር መሳሪያ እንዳይኖራት ለማድረግ ቆርጠናል። ኢራን ያለባትን አለማቀፍ ግዴታ እንድታከብር ለማሳመን ከተለያዩ የአለም ሀገራት ጋር እየሰራን ነው ።

የዩ ኢስ አሜሪካ ምክትል ፕሬዜደንት አካለውም ለፊሊስጤምና እስራኤል የሁለት መንግስታት መፍትሄ አማራጭ የለውም አይነት መልዕክት አስተላልፈዋል።

OTON ባይድን

ግቡ ወይም አላማው እንደሚታወቀው ከመጨረሻው ደረጃ ላይ ለመድረስ ነው። ሁለት መንግስታት መፍትሄ። ፊሊስጤም እና ኢስራኤል በሰላምና ደህንነት ጎን ለጎን የሚኖሩባቸው መንግስታት!

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በበኩላቸው የእስራዬልና የፍልስጤም የሰላም ድርድር መጀመሩ ጥሩ መሆኑን ገልፀዋል፤ ግን አድካሚና ከባድ እንደሚሆን አልሸሸጉም።

OTON ኔታንያሁ

መስተዳደሩ ( የኦባማ) በአካባቢው ሰላም ለማስፈን የሚያደርገውን ጥረት አደንቃለሁ። ይህ ከባድ እንደሆነ ይገባኛል። እናም ትልቅ ትዕግስት ይጠይቃል። ይሁንና እነዚህ ጥረቶች ፍሬ ማፍራት በመጀመራቸው ተደስቻለሁ። ይህን ግጭት ለማስወገድ የቀጥታ ድርድር መጀመር፦ ድርድሩን በቋሚነት መቀጠልና አላማ ያለው መሆን አለበት።

ባለፈው እሁድ የፊሊስጤም ነፃ አውጪ ድርጅት በምህፃሩ PLO ከእስራኤል ጋር ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር ለማድረግ ተስማምተዋል።

Lidet Abebe, Negash Mohammed

Audios and videos on the topic