የፖሮሼንኮ የብራሰል ጉብኝት | ዓለም | DW | 27.08.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የፖሮሼንኮ የብራሰል ጉብኝት

ሁለቱ ወገኖች ባልፀናው በዩክሬን የተኩስ አቁምና ኬቭ በተጋረጠባት የኤኮኖሚ ፈተናዎች ላይ ያተኮረ ውይይት ማካሄዳቸው ተዘግቧል ።የኬቭን መንግሥት የሚደግፈው የአውሮፓ ህብረት ሃገሪቱ ፖለቲካዊና ምጣኔ ሃብታዊ የተሃድሶ እርምጃዎችን እንድትወስድ ይፈልጋል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:32

የፖሮሼንኮ ጉብኝት

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ፔትሮ ፖሮሼንኮ ዛሬ ብራሰልስ ቤልጂግ ውስጥ ከአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ ። ፕሬዝዳንት ፖሮሼንኮ ፣ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ዦን ክሎድ ዩንከር እና ከአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ቱስክ ጋር በተለይ ባልፀናው በዩክሬን የተኩስ አቁምና ኬቭ በተጋረጠባት የኤኮኖሚ ፈተናዎች ላይ ያተኮረ ውይይት ማካሄዳቸው ተዘግቧል ።የኬቭን መንግሥት የሚደግፈው የአውሮፓ ህብረት ሃገሪቱ ፖለቲካዊና ምጣኔ ሃብታዊ የተሃድሶ እርምጃዎችን እንድትወስድ ይፈልጋል ። ስለዛሬው የፖሮሼንኮ የብራስልስ ቆይታ የብራሰልሱን ዘጋቢያችንን ገበያው ንጉሴን ስቱድዮ ከመግባታችን በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።

Audios and videos on the topic