የፖለቲካ ፓርቲዎች የድርድር አጀንዳ ጉዳይ | ኢትዮጵያ | DW | 20.06.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የፖለቲካ ፓርቲዎች የድርድር አጀንዳ ጉዳይ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር«ኢሕአዲግ» እና 16 ተቃዋሚ ፓርትዎች የሚደራደሩበትን 13 አጀንዳዎች ባለፈዉ ረቡዕ ማርቀቃቸዉ ተዘግቧል። አንድ አንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያቀረቧቸዉን ሌሎች አጀንዳዎች ግን ኢሕአዲግ ዉድቅ ማደረጉ ቅሬታ እንዳስነሳም ተጠቁመዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:05

ፓርቲዎች የድርድር

በትናንት ሰኞዉ ስብሰባ ተደራዳሪዎች ካረቀቋቸዉ 13 አጀንዳዎች ስድስቱን እንዳፀደቁት ተዘግቧል። ከስድስቱም የፀረ-ሽብር አዋጅ፣ የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማሕበራት አዋጅና የታክስ አዋጅ እንደሚገኝበትም ዘገባዉ ጠቅሰዋል።

15 አጀንዳዎች ማቅረባቸዉን የሚናገሩት የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሙሉጌታ አበበ እስካሁን የፀደቁትን ጨምሮ የፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ አዋጅ፣ የድሞክራሲ፣ የሰባዊ መብትና የፍትህ ተቋማት አወቃቀር ላይ ለመደራደር መስማታቸዉን ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። ዜጎች በክልል ተዛዙረዋዉ የመስራት መብት፣ የመሬት ሊዝ፤ ተፈናቃዮችንና ብሔራዊ መግባባትን በተመለከተም ሊደራደሩበት መስማታቸዉን አብራርተዋል። ፓርቲያቸዉ ያልተስማማበትና አቋም ሊቀይር የማይችልበት «ወሰኝ» አጀንዳዎች እንዳሉም የመኢአዱ ምክትል ፕሬዝደንት ይናገራሉ።

አቶ ሙሉጌታ ፓርቲያቸዉ ያቀረበዉን ቀሪ አጀንዳዎች ገዥዉ ፓርቲ ለመቀበል አቋሙን እንዳሳየ ገልፀዉ ቅዳሜ በሚቀጥለዉ ስብሰባ  ፓርቲያቸዉ አቋም ይዞ እንደሚገኝ ይናገራሉ።

ትላንትና በተደረገዉ ዉይይት የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ላይ ለመደራደር የቀረበዉን ረቅቅ «ኢህአዴግ ሀገሪቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ሆና ስለ አዋጁ መደራደር አልችልም» ሲል አጀንዳዉን ዉድቅ ማድረጉ ከአገር ዉስጥ የመጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የድንበር ወሰንን በተመለከተ በቀረበው ረቂቅ መንግስት ከጎረቤት ሃገራት ጋር ተመካክሮ የሚያካልል ጉዳይ እንጅ የፖለትካ ድርድር አጀንዳ የሚሆን አይደልም ሲል ኢህአዴግ አጀንዳዉን እንደማይዘዉ ተጠቅሰዋል። በሕገመንግስቱ ማሻሸያ ሊደረግበት ይገባል ተብሎ ከቀረቡት አንቀሶች፣ ማለትም አንቀፅ 39፣ አንቀፅ 72 እና አንቀፅ 46፣ ኢህአዴግ “በዚህ ጉዳይ ላይ የመደራደር መብት የፓርቲዎች አይደለም» ሲል አጀንዳዉን ዉድቅ ማድረጉ ዘገባዎቹ ያመለክታሉ።

አሁን የተጀመረዉ ድድር በሐገሪቱ ያለዉን ፖለቲካዊ ዉዝግብ ለማስወገድ ይረዳል ብለዉ ያስባሉ? ብለንም የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ ተከታታዮቻችንን ጠይቀን ነበር። በራያ አከባቢ ነዋሪ መሆናቸዉን የተናገሩት አቶ አሰፋ፣ የአባታቸውን ስም ሳይጠቅሱ፣ የድርድሩን መጀመር ጥሩ ነዉ ብለዉ  በገዢዉም ሆነ በተቃዋሚ ፓርቲዎች በኩል አለ ያሉትን ድክመት ይጠቅሳሉ።

«ኢትዮጵያ ውስጥ ተቃዋሚ የሚባል ነገር የለም። አጉል ጫጫታ ነው» ያሉ ሲኖሩ «ከድርድሩ የሚጠበቅ አንዳችም ነገር የለም እንደሌለም እራሳቸው ተደራዳሪወቹ ያውቃሉ አየሰሩ ነው እንዲባሉ እነጂ የኢተረዮጵያ መንግሥት  በድርድር አምኖ ለውጥ ያመጣል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው» የሚልም የፅሁፍ አስተያየት ደርሶናል።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሐመድ 
  
   


 

Audios and videos on the topic