የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ዕጩዎች | ኢትዮጵያ | DW | 21.05.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ዕጩዎች

የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ዕጩዎች

default

የፖለቲካ ፓርቲዎችና እጩዎች

በምርጫዉ ከሥልሳ-በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይካፈላሉ ወይም ይወዳደራሉ።ከተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በርካታ እጩዎቹን በማቅረብ የመጀመሪያዉን ሥፍራ የያዘዉ .የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ነዉ።-501 እጩዎች።ሁለተኛዉን ሥፍራ የያዘዉ ደግሞ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ)-421 እጩዎች አሉት።ሰወስተኛዉ የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ነዉ።319 እዎች አሉት።ብዙ እጩዎችን በማቅረብ አራተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘዉ የኢትዮጵያዉያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ነዉ።230 እጩዎች አቅርቧል።


የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 547 መቀመጫዎች አሉት።ለዚሕ ምክር ቤት አባልነት 2ሺሕ 2 መቶ አምስት እጩዎች ይወዳደራሉ።ከእጩዎቹ 27ቱ በግል የቀረቡ ሲሆን የተቀሩት በሙሉ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ናቸዉ።ለአካባቢ መስተዳድር (ክልል) ምክር ቤቶች አባልነት ደግሞ ከ4 ሺሕ ሰባት መቶ ሠላሳ በላይ እጩዎች ይወዳደራሉ።

*ምንጭ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ።
ነጋሸ መሐመድ

አርያም ተክሌ