የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅሬታና የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ምላሽ | ኢትዮጵያ | DW | 05.08.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅሬታና የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ምላሽ

ኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የአመራሮችና የአባላት እስራት እንዲሁም በተለያዩ አከባቢዎች የጽህፈት ቤቶቻቸው መዘጋት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴያቸው ላይ ፈተና መደቀኑን አስታወቁ፡፡በቅርቡ በክልሉ በነበረው አለመረጋጋት 16 አባላቶቹ መገደላቸውን ኦፌኮ ገልጿል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:24

አመራሮቻችን ታስረዉብናል

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የአመራሮችና የአባላት እስራት እንዲሁም በተለያዩ አከባቢዎች የጽህፈት ቤቶቻቸው መዘጋት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴያቸው ላይ ፈተና መደቀኑን አስታወቁ፡፡ በቅርቡ በክልሉ በነበረው አለመረጋጋት 16 አባላቶቹ መገደላቸውን ኦፌኮ ገልጿል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቃለ አቀባይ አቶ ቀጄላ መርዳሳ በበኩላቸው የፓርቲው አመራሮች መታሰራቸውን እና በሂደቱም ፓርቲው ጉዳዩን የመከታተል  መብት እስከማጣት መድረሱን አመልክተዋል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚዩንኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር በኩል የቀረበላቸውን አቤቱታ ተመልክተው ለአዲስ አበባ እና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽኖች ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸው፤ በኦፌኮ በኩል እስካሁን የደረሰን ቅሬታ የለም ብለዋል፡፡

ስዩም ጌቱ

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic