1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፖለቲካ ምሁርና የSPD ፖለቲከኛ ባለቤት

ሐሙስ፣ ጳጉሜን 5 2001

ዶክተር ምፅላል ክፍለ እየሱስ ይባላሉ ። በጀርመን በቱሪንገን ፌደራዊ ክፍለ ሀገር የአንጋፋው የጀርመን ሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ SPD ሊቀ መንበር የክሪስቶፍ ማቺ ባለቤት ናቸው ።

https://p.dw.com/p/JcXI
ዶክተር ምፅላል እና ባለቤታቸው ማቺምስል AP

በዚህ ፌደራዊ ክፍለ ሀገር በቅርቡ በተካሄደ ምርጫ ውጤት ሶስተኛ ደረጃ ያገኙት የSPD ው ክሪስቶፍ ማቺም በዚህ ግዛት በሚመሰረተው ተጣማሪ መንግስት ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን ከሚችሉት የፓርቲ መሪዎች አንዱ ናቸው ።የኚህ ታዋቂ የጀርመን ፖለቲከኛ ባለቤት ፣ ዶክተር ምፅላል ክፍለ እየሱስ በዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን የስራና የህይወት ልምዳቸውን ያካፍሉናል ። ሰፊውን ጊዜ ወደ ሚይዘው ወደ ዚህ ቃለ ምልልስ ከማለፋችን በፊት ስፓኝ ስራ አጥ የውጭ ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ስለጀመረችው መርሀ ግብር ጥቂት እናወሳለን ።

ሂሩት መለሰ