የፕ/ት ኡሁሩ ኬኒያታ ክስ መራዘም | አፍሪቃ | DW | 01.11.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የፕ/ት ኡሁሩ ኬኒያታ ክስ መራዘም

ትላንት ዘሄግ ኔዘርላንድ ውስጥ ያስቻለው ዓ/ዓቀፉ የወንጀል ፍ/ቤት በኬኒያው ፕ/ት ኡሁሩ ኬኒያታ ላይ የተያዘውን የክስ ሂደት እስከሚቀጥለው የካቲት ወር ድረስ ለሶስት ወር ማራዘሙን ኣስታወቀ። የኣፍሪካ ህብረት ግን በቂ ኣይደለም እያለ ነው።

የኣፍሪካ ህብረት በፕ/ት ኬኒያታ እና ምክትላቸው ላይ የተከፈተው የክስ ፋይል ለኣንድ ዓመት እንዲዘገይ መጠየቁ የሚታወስ ሲሆን በትላንትናው ዕለትም የህብረቱ ልዑካን በኒውዮርክ ከጸጥታው ም/ቤት አባላት ጋር ዝግ ስብሰባ ማድረጋቸው ታውቀዋል።

ኣንድ ጋዜጠኛን ጨምሮ የኬኒያው ፕ/ት ኡሁሩ ኬኒያታ እና ምክትላቸው ዊሊያም ሩቶ በሰብዓዊ ፍጡር ላይ በተፈጸመ ወንጀል የተከሰሱት ኣወዛጋቢውን የ2007 ቱን የኬኒያ ጠ/ምርጫ ተከትሎ በኣገቱ በተቀሰቀሰው እና በትንሹ 1100 ያህል ሰዎች ተገድለው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ የተፈናቀሉበትን ብጥብጥ ተከትሎ ነው። ሁለቱ ተከሳሾች ከወዲሁ በቀጣዩ ምርጫ የኬኒያ መሪዎች ሆነው ቢሰየሙም የICC ክስ ግን ይበልጥ ተጠናከረ እንጂ ኣልረገበም።

በዚሁ መሰረት ም/ፕ/ት ዊሊያም ሩቶ ባለፈው መስከረም ወር ኣጋማሽ ላይ ዘ ሄግ በሚገኘው ዓ/ዓቀፉ የወንጀል ችሎት መቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን የፕ/ቱ ዑሁሩ ኬኒያታ ቀጠሮ ደግሞ እ ኣ ዘ አ በፊታችን ታህሳስ 12 ቀን 2013 ዓ/ም እንዲጀመር ነበር የታሰበው።

የሽብር ጥቃቱንም እንደ ተጨማሪ መከራከሪያ ለሚጠቀሙት የኬኒያ መሪዎች እነሱ ለቀጠሮ ችሎት የሚመላለሱ ከሆነ በዚያች ኣገር ሊከሰት የሚችለውን የዓመራር ክፍተት በመጠቆም የኣፍሪካ ህብረትም ሆነ የኣፍሪካ መሪዎች ICC ን ሲሟገቱ ቆይቷል።

የኣፍሪካ መሪዎች ፍላጎት እ ኣ ዘ ኣ ጥቅምት 12 ቀን 2013 ለተ መ ድ የጸ/ጥ/ም/ቤት በጻፉት ደብዳቤ መሰረት የኬኒያታ ክስ ቢያንስ ለኣንድ ዓመት እንዲራዘም የሚጠይቅ ሲሆን ICC ግን እስከ ትላንት ከዓቐሙ ፍንክች ሳይል ቆይቶ ነበር።

ትላንት የኣፍሪካ ህብረት የሚኒስትሮች ልዑካን ቡድን በኒውዮርክ ከተ መ ድ የጸ/ጥ/ም/ቤት አባላት ጋር በዝግ እየተወያዩ በነበረበት ወቅት ዘ ሄግ ያስቻለው ዓ/ዓቀፉ ፍ/ቤት ICC ግን ለ AU ጥያቄ ይሁንታ ሊባል ባይችልም እምቢም ሳይል አጭር የእፎይታ ጊዜ ፈቅዷል። የኬኒያታን ፋይል እ ኣ ዘ ኣ እስከ የካቲት 5 ቀን 2014 ድረስ ለሶስት ወር በማራዘም። ምክኒያቱ ደግሞ ኬኒያዊው የፖለቲካ ተንታኝ ፕ/ር ፒተር ካጉዋንጃ ኢንደሚሉት

ምክትላቸውን ለመነጣጠል። ይሄ ኣንደኛው ነው። ሁለተኛ ደግሞ የም/ፕሬዝደንቱ ክስ ICC የ ከፋፍሎ መምራት ዓይነት ሚና ነው የሚጫወተው። ፕሬዝደንት ኬኒያታን እና ኣስቀድሞ ለታህሳስ ተቀጥረዋል። ለዚህ ነው ይሄኛው ተሻግሮ ወደ የካቲት የተላለፈው። ሌላው ደግሞ ICC ከኣፍሪካ ህብረት የበረታበትን ጫና መቐቐም ይኖርበታል። እንዲያውም ዛሬ የህብረቱ ቡድን የኬኒያታን እና የሩቶን ጉዳይ ከጸጥታ ጥበቃው ም/ቤት አባላት ጋር ለመምከር ስብሰባ ተቀምጠዋል።

የኣፍሪካ ህብረት ልዑካንን የመሩት የኢትዮጵያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ ኣድኃኖም ከውይይቱ በሗላ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት ከሆነ ደግሞ የተሰጠው የሶስት ወር ጊዜ በቂ ኣይደለም። ኣፍሪካውያኑ ለጸ/ጥ/ም/ቤት ያቀረቡት ለኣንድ ዓመት የማራዘም ጥያቄ ሊፈቀድ ይገባል ያሉት ሚኒስትሩ ከም/ቤቱ ዓባላት ደጋፊዎች እንዳሉ ሁሉ በጉዳዩ ላይ ችግር ያለባቸ ደግሞ ይኖራሉ በማለትም ለመውቀስ ሞክረዋል።

ትላንት ዘ ሄግ የቀረቡት የኬኒያታ ጠበቆችም መሆኑ ካልቀረ ቀጠሮው የካቲት 5 ሳይሆን 14 እንዲሆንላቸው ጠይቀው ነበር። ዳኞቹ ግን ኣልተቀበሉትም። የICC ዓቃቢያነ ህግጋቱ ግን ቀነ ቀጠሮውን ሳይቃወሙ ወቷል። ምክኒያቱም ፕ/ር ካጉዋንጃ እንደሚሉት ተጨማሪ ማስረጃ ከማሰባሰብ ጎንለጎን ከኬኒያታ ተከላካይ ጠበቆች በኩል የቀረቡትን የመከላከያ ጭብጦች ለመመርመር ጭምር ጊዜ ያገኛሉና። ችሎቱም ቢሆን ፕ/ር ፒተር ካጉዋንጃ እንደሚሉት ጉዳዩን በቀጠሮ ማጘተቱን የጠላው ኣይመስልም።

ችሎቱ የሚያደርገው ዋናው ስልታዊ ኣካሄድ ህጉንም ሳይስት በኣፍሪካ ህብረት እና በዓለም ዓቀፉ ፍ/ቤት ብሎም በጸጥታ ጥበቃው ም/ቤት መካከል የተፈጠረውን ልዩነት እንደዚህ እያስታመመ ከተቻለም ለመቅረፍ ነው። ልብ በል ቀነ ቀጠሮው የካቲት 5 ማለት የሚውለው በጥር ከሚካሄደው የኣፍሪካ ህብረት ጉባዔ በኃላ መሆኑ ነው። ስለዚህ ህብረቱ በICC ላይ ከወዲሁ ዳግም ተጨማሪ ውሳኔ ሊያስተላልፍ ኣይችልም ማለት ነው።

የኣፍሪካ መሪዎችም ሆኑ ህብረቱ ዓ/ዓቀፉ ችሎት በኣፍሪካ መሪዎች ላይ በተለይ ኣነጣጥሮ እየሰራ ነው ሲሉ ይከሳሉ። በእርግጥም ኣሁን ICC የያዛቸው ስምንት ያህል የወንጀል ፋይሎች በሙሉ ከኣፍሪካ የመጡ ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል አራቱ ግን በራሳቸው በኣፍሪካ መንግስታት ለችሎቱ የተመሩ ናቸው።

ጃፈር ዓሊ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic