የፕሮፌሰር አምሳሉ አክሊሉ ማስታወሻ | ባህል | DW | 23.12.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የፕሮፌሰር አምሳሉ አክሊሉ ማስታወሻ

ብዙዎቻችን በመዝገበ ቃላታቸው ተምረናል። አልያም በአስተማሪ እና ደራሲነታቸው እናውቃቸዋለን። ፕሮፌሰር አምሳሉ አክሊሉ።

እኚሁ ምሁር በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ፕሮፌሰር አምሳሉ እንዴት ይታወሳሉ? እሳቸውን በጓደኝነት፣ በአስተማሪ እና በኋላም በስራ ባልደረባነት የሚያውቋቸው ሁለት መምህሮች ስለሳቸው አጫውተውናል። የመጀመሪያው በአዲስ አበባ ዮንቨርሲቲ የእንግሊዘኛ እና የስነፁሁፍ መምህር የነበሩና አሁን በጡረታ ላይ የሚገኙት ዶ/ር ኃይሉ አርዓያ ናቸው። ፕሮፌሰር አምሳሉን በጓደኝነት እንዲሁም በስራ ባልደረባነት ያውቋቸው ነበር።

በአሁኑ ጊዜ በጀርመን ሀምቡርግ ዮንቨርስቲ የአማርኛ እና የአፍሪቃ ስነ-ቃል መምህር ዶ/ር ጌቴ ገላዬም ፕሮፌሰር አምሳሉ በተለይ ለአማርኛ ቋንቋ ማዳበር ትልቅ አስተዋፅዎ ያደረጉ ኢትዮጵያዊ ናቸው ይላሉ።

ፕሮፌሰር አምሳሉ ከኢትዮጵያ ውጪ እኢአ ከ1997-2002 ዓም በሀምቡርግ ዮንቨርስቲ በአፍሪቃ እና ኢትዮጵያ የትምህርት ጥናቶች የትምህርት ክፍል ውስጥ የአማርኛ እና የግፅዝ መምህር ሆነው ካገለገሉ እና ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላም ሌሎች መፅሀፎችን ፅፈዋል። ፕሮፌሰር አምሳሉ ወደ 40 ዓመት የሚጠጋ እድሜያቸውን በማስተማር፣ ተማሪዎችን በማማከር እንዲሁም ጥናትና ምርምር በማድረግ ያገለገሉ ምሁር እንደነበሩ ከተማሪነት ጊዜያቸው ጀምረው የሚያውቋቸው ዶ/ር ጌቴ ገልጸውልናል።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic