የፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ የምክር ቤት ውሏቸው ትችት | አፍሪቃ | DW | 14.09.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ የምክር ቤት ውሏቸው ትችት

የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ በትናንትናው የምክር ቤት ውሏቸው የኤኮኖሚ ነጻነት ታጋዮች ፓርቲ አባላት ዘለፋ እና ውንጀላ ገጥሟቸዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:53

የፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ የምክር ቤት ውሏቸው ትችት

ፕሬዝዳንቱ በተደጋጋሚ ንግግራቸውን ለማቋረጥ የተገደዱ ሲሆን «ወንጀለኛ» እና መሰል ዘለፋዎችም ገጥሟቸዋል። አነጋጋሪው የኤኮኖሚ ነጻነት ታጋዮች ፓርቲ መሪ ጁሊየስ ማሌማ ፕሬዝዳንቱ ስልጣናቸውን እስኪለቁ እስከመጠየቅ ደርሷል። በምክር ቤቱ ጃኮብ ዙማ በመንግስታቸው እና ፓርቲያቸው መካከል ተፈጥሯል ስለሚባለው ትንቅንቅ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። ደቡብ አፍሪቃ የሚገኘው የዶይቼ ቬለ ወኪል መላኩ አየለ ተጨማሪ ዘገባ አለው።

መላኩ አየለ

እሼቴ በቀለ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic