የፕሬዝዳንት ምርጫ ዋዜማ በኮንጎ | የጋዜጦች አምድ | DW | 27.10.2006
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የጋዜጦች አምድ

የፕሬዝዳንት ምርጫ ዋዜማ በኮንጎ

በመጭዉ እሁድ በኮንጎ በሚደረገዉ ሁለተኛ ዙር ፕሪዘዳንታዊ የማጣርያ ምርጫ በፕሪዝደንት ካቢላ እና በተቀናቃኛቸዉ ዣንፔር ቤንባ መካከል ተሸናፊ የሚኖር አይመስልም

ለምርጫዉ መስተንግዶ

ለምርጫዉ መስተንግዶ

ካቢላም በበኩላቸዉ የአሸናፊነቱን ቦታ እንደያዙ በግልጽ ሲያስቀምጡ ዣምፔር ቤንባ ደግሞ የሪፐብሊኩ ፕሪዝደንት እንደሆኑ በማስተጋባት ላይ ናቸዉ። በመዲናዋ ኪንሻሳ እንደገና ከባድ ግጭት ይነሳል የሚል ስጋት አለ። ሰላም አጥቶ ባለዉ አንዳንድ የአገሪቷ ክልል ደግሞ፣ ይህ የምርጫ ዉጤት የቤንባን ወይም የካቢላን መሸናነፍ ብቻ ሳይሆን፣ ምርጫዉ ሰላም አልያሞ ጦርነት ያስከትላል ነዉ ስጋቱ! Wim Dohrenbusch በቦታዉ ተገኝቶ እንደዘገበዉ

ገና ማጣርያ ምርጫዉ ሳይጀመር የፕሪዝደንት ካቢላ ወጣት ደጋፊዎች ተሰብስበዉ፣ ሞተር ብስክሌት ያላቸዉም፣ በአቧራማዉ መንገድ ላይ ልጃገረዶችን እና ሴቶችን ከዃላ አፈናጠዉ ጆሴፍ ካቢላ እንዳሸነፉ ያህል በአደባባይ ሆ! እያሉ በሞተር ሳይክል ሲበሩ፣ መሃል የጆሴፍ ካቢላ ተቀናቃኝ፣ የዣምፔር ቤንባ ፎቶ በትልቁ ተለጥፎ ሲያጋጥም የነቀፊታ ጩኸት መሰማት ይጀምራል። ቹኸቱ እና ብጥብጡ ይደራል። ለደጋፊ መሰብሰብያ እገዛ እንዲሆን የተሰቀለዉን የጆሴቭ ካቢላን ፎቶ በጩኸት አዉርደዉ የሚጥሉት ያህል!

ምስራቅ ኮንጎ፣ በሰሜን ኪቩ ክልል ከሶስት ወራት በፊት በተካሄደዉ ፕሪዝደንታዊ ምርጫ፣ ካቢላ 80% የአብልጫ ድምጽ ማግኘታቸዉ ይታወሳል። የቀድሞ አማጺ እና አባት አገርን ለወጡ የሚባሉት ዣንፔር ቤንባ ከጎረቤት ኡጋንዳ እና ሩዋንዳ ድጋፍ የአራቸዉን መንግስት በመዉጋታቸዉ ፣ አሁን በሚካሄደዉ ምርጫ ቀላል ሁኔታን አላመቻቸላቸዉም።

በኮንጎ ጦርነት መቆሙ በይፋ ከታወቀ አራት አመታትን ቢያስቆጥርም፣ በበምስራቃዊው የአሪቷ ክፍል፣ እስከ አሁን፣ ሰላምን በተመለከተ፣ ርዕስ እንኳ መሆን አልቻለም። በአሁኑ ወቅት 10,000 የሚሆኑ ሁቱስ የተባሉት የሩዋንዳ ብሄሮች በኮንጎ ሸፍተዉ ሲገኙ፣ ከነዚህ መካከል ከ12 አመት በፊት በሩዋንዳ የህዝብ ፍጅት ያደረሱት ኢንተር ሃምዌ፣ የተባሉት አማጺ ሚሊሽዎች ይገኙበታል። የሁቱስ ብሄር ለፈጸመዉ ወንጀል በኮንጎ የሚገኙት ቱትሲ በመባል የሚታወቁት አማጽያን ሁቱትስን ለመበቀል ፍላጎት አላቸዉ የሚል እምነት እና ስጋትም አላቸዉ። አንድ የኮንጎ ተወላጅ
«እነዚህ ኢንተር ሃምዌ የተባሉት አማጺ ቡድኖች ህዝብን ማስፈራራታቸዉን ከቀጠሉ መሳርያችንን በምንም አይነት አንፈታም። መንግስት ለህዝብ ደህንነት እና ጥበቃ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ስለማያደርግ፣ እኛ ለህዝቡ ጥበቃ እና ከለላ እንቆማለን!»

ባለፈዉ ሳምንት በፕሪዝደንት ካቢላ እና በቀድሞዉ አማጺ መሪ ዣንፔር ቤንባ ደጋፊዎች መካከል ከባድ ዉጥረት እና ግጭት በተደጋጋሚ ታይቶአል። በመጭዉ እሁድ በመዲናይቷ ኪንሻሳ በሚካሄደዉ ፕሪዝደንታዊ የማጣርያ ምርጫ ላይ፣ የተባበሩት መንግስታት መልክተኛ ሁለቱ ኦጩዎች ደጋፊዎቻጨዉ ሁከት እዳይፈጥሩ መግልጽ ማስራዳት እንዳለባቸዉ በሳምንቱ መጀመርያ ላይ መጠየቁም ታዉቋል።

ተዛማጅ ዘገባዎች