የፕሬዚዳንት ኦባማ ዳግመኛ ጉብኝት በበርሊን | ዓለም | DW | 17.06.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የፕሬዚዳንት ኦባማ ዳግመኛ ጉብኝት በበርሊን

የዩናይትድ እስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ፤ በጥቅምት ወር ማለቂያ ገደማ፤ 2001 ለመጀመሪያ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት እጩ ተወዳዳሪ ሆነው ከመቅረባቸው ጥቂት ወራት ቀደም ሲል በሐምሌ ፤ 2000 ዓ ም፤ በርሊንን ጎብኝተው እንደነበረ የሚታወስ ነው ።

ያኔ፤ ከ 200,000 የማያንስ ህዝብ ፣ በጋለ ስሜትና አድናቆት አቀባበል በማድረግ ንግግራቸው ማዳመጡ የሚታወስ ነው። ኦባማ ፤ ነገ ማታ በርሊን ገብተው ፤ በማግሥቱ በብራንደንቡርግ በር ንግግር የሚያሰሙ ሲሆን ፤ እንደያኔው ህዝቡ በጋለ ስሜት ያዳምጠቸዋል ተብሎ እንደማይታሰብ ነው የሚነገረው። ስለአሁኑ ጉብኝት ዓላማ ፣ የሁለቱ መንግሥታት መሪዎች ፣ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና የጀርመን መራኀተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ስለሚያተኩሩባቸው ዐበይት ጉዳዮች ፣የበርሊኑን ዘጋቢአችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን በስልክ አነጋግሬው ነበር።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic