የፕሬዚዳንት አልሲሲ የሰሞኑ ዛቻና አንድምታው | ኢትዮጵያ | DW | 01.04.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የፕሬዚዳንት አልሲሲ የሰሞኑ ዛቻና አንድምታው

የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ የግብፅ ጠብታ ውኃ ከተነካ አካባቢው ቀውስ ያስተናግዳል ሲሉ የመንግስታቸውን አቋም አንፀባርቀዋል። ይህ የግብፅ አቋም አንድም የማስፈራራት ፣ በሌላ በኩል ከውኃ ሙሌቱ በፊት በኢትዮጵያ ላይ ጫና የማሳደር ዓላማ ያለው መሆኑን ያነጋገርናቸው ሁለት የዘርፉ አዋቂዎች ተናግረዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:15

የግብጹ ፕሬዚዳንት ንግግር ምን አንድምታ አለው?

ኢትዮጵያ በመጪው ክረምት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት እንደምታከናውን መንግሥት አሳውቋል። ይህንን ተከትሎ የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ «የግብፅ ጠብታ ውኃ ከተነካ አካባቢው ቀውስ ያስተናግዳል» ሲሉ የመንግሥታቸውን አቋም አንፀባርቀዋል። ይህ የግብፅ አቋም አንድም የማስፈራራት ፣ በሌላ በኩል ከውኃ ሙሌቱ በፊት በኢትዮጵያ ላይ ጫና የማሳደር ዓላማ ያለው መሆኑን ያነጋገርናቸው ሁለት የዘርፉ አዋቂዎች ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በውስጥ አንድነቷ ፀንታ ሥራዋን መቀጠልና የሚመጣን ጫና መቋቋም ይገባልም ብለዋል ባለሙያዎቹ። በኢትዮጵያ ሱዳንና ግብፅ መካከል ሲደረግ የቆየው የረጅም ጊዜ ድርድር ከተቋረጠ ሰነባብቷል። የኢትዮጵያን ድንበር ጥሳ በመግባት ወረራ መፈፀሟ የተነገረው ሱዳንም ከግብፅ ጋር ወታደራዊ ልምምድ በማድረግ ድርድሩ እንዲጓተት እያደረገች መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥት የግብፅ ፕሬዚዳንት ንግግር ላይ ግን እስካሁን ያለው ነገር የለም።

ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ
ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic