የፕሬስ ይዞታ በኢራን | ዓለም | DW | 17.06.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የፕሬስ ይዞታ በኢራን

የኢራን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት ያስከተለው ውዝግብ ሀገሪቱን ከፍተኛ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ከቷል ። የቀውሱ ሰለባ ከሆኑት ውስጥ ነፃው ፕሬስ አንዱ ነው ።

default

ለሶስት አስርት ዓመታት በሀይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ ምክንያቶች የፕሬስ ቅድመ ምርመራ በሚካሄድባት በኢራን የአንዳንድ ዓለም ዓቀፍ ነፃ መገናኛ ብዙሀን ስርጭቶች እንደታገዱ ነው ከነዚህም ውስጥ ዶይቼቬለ በሀገሪቱ ቋንቋ በፋርስኛ ከቦን የሚያስተልፈው የራድዮ ስርጭት ይገኝበታል በኢራን ኢንተርኔትም የታገደ ቢሆንም በአሁኑ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ኢራናውያን በተለያዩ ዘዴዎች በኢንተርኔት ድረ ገፆችና ንዑሳን ድረገፆች ሀሳባቸውን ሲገልፁ እና መልዕክቶቻቸውንም ሲያስተላልፉ ከርመዋል ይህ በእጅጉ ያሰጋው መንግስት በሀገሪቱ ውጥረት ያሰፍናሉ ያላቸው መረጃዎች ከየድረ ገፆች ላይ እንዲነሱ አስጠንቅቋል በኢራን የፕሬስ ይዞታ ላይ በማተኮር የዶይቼቬለው ማትያስ ፎን ሀይም ያቀረበውን ዘገባ ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች

ሂሩት መለሰ/አርያም ተክሌ