የፕሬስ ነፃነት ቀን | ዓለም | DW | 03.05.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የፕሬስ ነፃነት ቀን

የፕረስ ነፃነት እና የጋዜጠኞች ደሕንነት ዘንድሮም እንደከዚሕ ቀደሙ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፕረስ ነፃነትና የጋዘጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቾች አስታወቁ። ይህን እለት በማስመልከት ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ድርጅት ያወጣዉ ዘገባ እንዳሳየው፤ በብዙ አገሮች መረጃ በነፃ ለማኅበረሰቡ ማሰራጨት ለጋዜጠኞች ይበልጡን አስቸጋሪ እየሆነ መጥቶአል።

የመገናኛ ዘዴዎችና የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ዛሬ የዋለዉን የፕረስ ነፃነት ቀንን አስታከዉ ባወጧቸዉ መግለቻዎች እንዳሉት ጋዜጠኞች ዛሬም ይገደላሉ፤ ይታሠራሉ፤ከሥራ ይባረራሉ፤ ይሰደዳሉም።የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎችም ተዘግተዋል።የጋዜጠኞች (መብት) ተከላካይ ኮሚቴ (CPJ) በምሕፃሩ እንደዘገበዉ ባለፈዉ ታሕሳስ ማብቂያ ባበቃዉ በጎርጎሪያኑ 2015፤ 72 ጋዜጠኞች ተገድለዋል።አምስተኛ ወሩን በያዘዉ በ2016 ደግሞ 10 ጋዜጠኞች ተገድለዋል።ከኢትዮጵያ እስከ ቻይና፤ ከኤርትራ እስከ ቱርክ፤ ከግብፅ እስከ ሶሪያ ባሉ ሐገራት በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች አንድም ታሥረዋል፤ ተከሰዋል፤ ከሥራ ተባርረዋል፤ አለያም ተሰድደዋል።የመብት ተሟጋቾች የኢትዮጵያ መንግሥት የፕረስ ነፃነትን ከሚያፍኑ መንግሥታት አንዱ መሆኑን በተደጋጋሚ ይናገራሉ።በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና የኮሙኒኬሽን ክፍለ-ትምሕርት ሐላፊ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ እንደሚሉት ግን ኢትዮጵያ ዉስጥ ሥለ ፕሬስነፃነት መናገር ይቻላል።

አምናና ዘንድሮ በርካታ ጋዜጠኞችን ከሥራ በማገድ ቱርክ የመጀመሪያዉን ሥፍራ ይዛለች።720።የዓለም የፕሬስ ነፃነትን ዕለትን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ሐገራት የጋዜጠኞች ማሕበራት፤ CPJ፤ ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች እና ሌሎች የመብት ተሟጋች ድርጅቶችም መንግሥታት፤ ድርጅቶችና ቡድናት ሕዝብ መረጃ የማግኘት መብቱን እንዲያከብሩ አሳስበዋል።

የበርሊኑ ወኪላችን ዛሬ ታስቦ ስለዋለዉ የፕሬስ ነፃነት ቀን የዶይቼ ቬለ ጋዜጠኞች ያሰባሰቡትን አስተያየት አጠናቅሮ ልኮልናል።


ይልማ ኃ/ሚካኤል

ነጋሽ መሃመድ

አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic