የፕሬስ ቀን በኢትዮዽያ | ኢትዮጵያ | DW | 04.05.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የፕሬስ ቀን በኢትዮዽያ

ዛሬ በአለም ዙሪያ የፕሬስ ነፃነት ቀን ታስቦ ውሏል። በርካታ ለፕሬስ ተሟጋች የሆኑ ድርጅቶች የኢትዮጵያን የፕሬስ ነፃነት ይዞታ፤ ጥያቄ ውስጥ ከተዋል።

default

በተለይም ቅርብ ጊዜ « Freedom Housse“ የተባለው የፕረስ ተሟጋች ድርጅት፤ ኢትዮጵያ ለፕረስ ነፃነት ከማያሰጉ ወደ ሚያሰጉ አገሮች መመደቧን ማስታወቁ ይታወሳል። ሰኞ ዕለት ደግሞ ዓለም ዓቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ሲፒጄ ኢትዮዽያ ኢንተርኔትን ከሚያቅቡ 10 ሀገሮች አንዷ ሲል የኮነነበትን መግለጪያ አውጥቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ዛሬ በአዲስ አበባ ሲደረግ የነበረው የዓለም የፕሬስ ቀን መታሰቢያ ስብሰባ ውዝግብ ገጥሞታል። ስብሰባው በመንግስት ሆን ተብሎ ተበጥብጧል በማለት የግሉ ፕሬስ አባላት ሲወቅሱ፤ መንግስት በበኩሉ በሰላም እየተካሄደ ነው ይላል። ልደት አበበ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ነፃ የመገናኛ ብዙሀን ቀኑን በምን አይነት ሁኔታ እንደሚያከብሩ ፤ የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የሆኑትን አቶ ዳዊት ከበደን እንዲሁም ከመንግስት በኩል አቶ ሽመልስ ከማልን አነጋግራለች።

ልደት አበበ

መሳይ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ