የፕሪቶርያ አስተዳደር ምርጫ እጩ ስያሜና ተቃውሞው | አፍሪቃ | DW | 27.06.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የፕሪቶርያ አስተዳደር ምርጫ እጩ ስያሜና ተቃውሞው

በደቡብ አፍሪቃ በየአምስት ዓመቱ ለሚካሄደው የአካባቢ ምክር ቤት ምርጫ ገዢው የአፍሪቃውያን ብሔረተኞች እንቅስቃሴ፣ «ኤ ኤን ሲ» ከጥቂት ጊዜ በፊት ለፕሪቶርያ ወይም በአገሬው አጠራር፣ ለጽዋኔ ከተማ የከንቲባነቱ ቦታ ቶኮ ዲፒዛን እጩ አድርጎ መሰየሙን ባለፈው ሳምንት ይፋ ካደረገ በኋላ በከተማይቱ ብርቱ ግጭት ያስከተለ ተቃውሞ መቀስቀሱ ይታወሳል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:06

«ኤ ኤን ሲ» የገጠመው ችግር

ሕዝቡ የገዚውን ፓርቲ ውሳኔ የተቃወመው በደርባን የተወለዱት ዲፒዛ ስለአካባቢው በቂ እውቀት የሌላቸው እና ውሳኔውም ያካባቢ የ«ኤ ኤን ሲ» ቅርንጫፎችን ፍላጎት ያላገናዘበ ነው በሚል ነው። ባለፈው ሳምንት በተፈጠረው ብጥብጥ እና ሁከት ተሽከርካሪዎች እና የውጭ ተወላጆች መደብሮች በእሳት ጋይተዋል፣ ብዙ ንብረት ጠፍተዋል፣ በዚሁ ወቅት ቢያንስ አራት ሰዎችም ሞተዋል። ፖሊስም የውጭ ዜጎች መደብሮችን ዘርፈዋል ያላቸውን 40 ተጠርጣሪዎች አስሮዋል። ሁኔታዎች በአሁኑ ጊዜ ምን ላይ እንደሚገኙ ጆሀንስበርግ የሚገኘውን ጋዜጠኛ መላኩ አየለን በስልክ ጠይቀነዋል።

መላኩ አየለ

አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic