የፕረስ ይዞታ በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 13.08.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የፕረስ ይዞታ በኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ መንግስት የታሠሩ ጋዜጠኞችን ነፃ መልቀቅ ይገባዋል ይላል ሲል አለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት በእንግሊዘኛ ምህፃሩ CPJ አሳሰበ።

Logos des Committee to Protect Journalists (www.cpj.org), eine weltweit agierende NGO mit Sitz in New York, die für den Schutz von Journalisten und für Pressefreiheit kämpft.

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ CPJ ባወጣው መግለጫ ጉዳዩ እንዳሳሰበዉ በመጥቀስ የበርካታ ጋዜጠኞችን ስም ዘርዝሮ በአሁኑ ሰዓት የሚገኙበትን ሁኔታ ፅፏል። የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅም እንዲሁ ጋዜጣዉን ማተም እንዳልተቻለና ክስ እንደቀረበበት አመልክቷል።

CPJ ባወጣው ዘገባ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን ዋቢ አድርጎ እንደገለፀው፤ በሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚደረገው እንቅስቃሴ ሽፋን እንዳያገኝ  የሙስሊም ጉዳዮችን የሚዘግቡ ጋዜጦች  ኢላማ ሆነዋል። ሀገር ዉስጥ የሚገኙ ምንጮቹን የጠቀሰዉ CPJ ለዚህ ምክንያቱ፤ በሙስሊም ጋዜጠኞች ላይ የሚፈፀመዉ እንግልት፤ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት መንግስት በሀይማኖት ጉዳዮች ላይ ጣልቃ አይግባብን የሚለው የሙስሊሙ ኅብረተሰብ ተቃውሞ ሽፋን እንዳያገኝ ሆን ተብሎ የሚደረግ ሙከራ መሆኑንም ፅፏል። ለዚህ ማሳያም የሙስሊሞች ጉዳይ የተሠኘችዉ ጋዜጣ አዘጋጅ ዩሱፍ ጌታቸው ፖሊስ ከቤት ከወሰዳቸው ጋዜጠኞች አንዱ መሆናቸዉንም ገልጿል።  የCPJ የአፍሪቃ ጉዳዮች ተመራማሪ ቶም ሮድስን ስለጋዜጠኞች እስራት እና የጋዜጦች የህትመት እገዳ በሚመለከት ስላላቸው መረጃ ተጠይቀው ሲመልሱ፤

business conference microphones © picsfive #17388450

የፕረስ ይዞታ በኢትዮጵያ

« በርካታ እገዳዎች ያሉ ይመስላል ማለት አሳታሚዎች በመንግስት ቁጥጥር ስር በመሆናቸው፤ ማተሚያቤቶች  በቀላሉ እንዳይታተሙ ያደርጋሉ። በቅርቡ እንዳይታተሙ የታገዱት የሙስሊሙ ጉዳይ ላይ የሚያተኩሩ ናቸው።  እንደምገምተው እነዚህ ጋዜጦች ሆን ተብለው የታገዱት  በአገሪቷ ላይ  ተስፋፍቶ ስላለው የሙስሊሙ  ተቃውሞ ሰፊ ሽፋን ስለሰጡ ነው። »

የህትመት እገዳ ከተደረገበት ጋዜጣ አንዱ የፍትህ ጋዜጣ ነው። የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ  በቅርቡ ስለገጠመው ሌላ ጫና ባጭሩ ገልፆልናል። በጉዳዩ ላይ ስጋት እንደገባው የገለፀው CPJ በዘገባውእንዳወጣውከኢትዮጵያባለስልጣናትበዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ ለማግኘትየሞከረቢሆንምእንዳልተሳካለት ነበር።ምናልባት በመካከሉመልስአግኝተውእንደውቶምሮድስንጠይቄያቸዋለሁ፤

«አላገኘንም።ታውቂያለሽትንሽተስፋአስቆራጭነው።ከማስታወቂያሚንስቴርየሚመለከታቸውንለማግኘትሞክሬያለሁ።ግን እስካሁን ድረስ ዝም እንዳሉ ነው። እንደሚመስለኝ የበለጠ ባለስልጣናቱን ለማግኘት መጣር አለብን። »

ኢትዮጵያ ውስጥ መቋቋሙ የተገለፀዉ የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ምናልባት አሁን ችግር እንዳንዣበበበት ለገልፁት የፕረስ ይዞታና የጋዜጠኞች የሥራ ሁኔታ የሚረዳዉ ይኖር ይሆን? « ስለ ፕረስ ምክር ቤቱ  አስተያየት ለመስጠት ገና አጭር ጊዜ ነው። እስከሚደራጅ የተወሰነ ጊዜ ይፈጃል። ትንሽ መጠበቅ እና መመልከት ያለብን ይመስለኛል።» ቶም ሮድስ

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic