የፕረስ ነፃነት እና መንግሥታት | ዓለም | DW | 03.05.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የፕረስ ነፃነት እና መንግሥታት

የፕሬስ ነጻነትን ማንም እንዳይደፍረው ና እንደይረገጠው ነቅተን መጠብቅ አለብን! ዛሬ የፕሬስ ነጻነት ቀን ነው፡፡እንዲህ ዓይነቱ ቀን መኖሩ መልካም ነው፡፡ቢያንስ በዓለም አቀፍ ደረጃ  ይህ የሰው ልጆች ሁሉ የትም ይኑሩ፣ የትም ይሁኑ የመናገርና የመጻፍ መብታቸው፣በአመት አንዴ በትልቅ ደስታ በያለበት ሲከበር እጅግ ደስ ያሰኛል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 05:45

የዓለም የፕረስ ቀን

 ለአንዳንዶቹ ይህ „ የፕሬስ ነጻነት ቀን“ ለይስሙላ ከንፈራቸውን እየመጠጡ ፣እየተሳለቁ አብሮ ለማክበር -መገመት እንደሚቻለው-ለእነሱ የሚያመች ቀን ይመስላቸዋል፡፡ ከልባቸው እንደ አልሆነ ግን ማንም ሰው ያውቀል፡፡
በአመት አንዴ ይህ ቀን ሲከበር የተቀሩትን ሦስት መቶ ስድሣ አራት ቀናት ደግሞ ፣እነሱን ሳይሰጨንቃቸው ፣ ዞር ብለው እንኳን አንድም ቀን መለስ ብለው ሳያስታውሱት  ያልፉታል፡፡ ለዚህ ደግሞ በርካታ ማሥረጃዎችን አንስቶ ለእነሱ መቁጠር ይቻላል፡፡ „የኢኮኖሚን ጥቅም ማስከበር የሚለውን አነጋገራቸውን እስቲ አገላብጠን እንመልከተው!
ይህን በቀላሉ ለመረዳት ዲሞክራቶች  ናቸው የሚባሉ የታወቁ የአውሮፓ ፖለቲከኞች ለቻይና መንግሥት እነሱ የሚያሳዩትን መሽቆጥቆጥ ዞር ብሎ መመልከት እሱ ብቻውን በቂ ምሥክር ነው፡፡
„የፕሬስ ነጻነት“ የሚባል ነገር እዚያ በቻይና እንደሌለ ሁሉም ሰው ያውቃል፡፡ አልፈው ተርፈውም ፣ቻይናዎቹ ነጻውንና ወገናዊነቱ ለማንም ያልሆነውን የእኛን ጣቢያ ፣ ዶቸ ቬሌን እና ሌሎችቹን የራዲዮ ጣቢያዎችን ሰው እንዳይሰማውና እዚያ እንዳይሰራጩ - የቻይና መንግሥት እዚያ አፍኖ ሲከለክል ፣ፊት ለፊት እንደመናገር በተዘዋዋሪ፣ እግረመንገዳቸውን ጠቀስ አድርገው የሚያልፉ የአውሮፓ ፖለቲከኞች ቁጥር ብዙ ነው፡፡ እራሳቸውም በኢኮኖሚው መስኩ ላይ ተሰማርተው ለጥቅማቸው ሲሉ የሚንቀሳቀሱ በአለ-ጸጎች ፣ የሰበአዊ መብቶች እዚያ ቻይና አገር ውስጥ ቢከበሩ፣ባይከበሩ ፣ሲረገጡም እያዩ፣ እስከዚህም ድረስ እነሱ አይጨነቁም፡፡እንዲያውም ለአንዳንዶቹ ቅንጣት ያህል ዴንታም ነገሩ አይሰጣቸውም፡፡ እንደዚህ ዓይነቱን የአውሮፓን አቋም ቻይናዎች ደግሞ በደንብ ያውቁታል፡፡
ቻይና ውስጥ ብቻ አይደለም! 
በሩሲያም ተመሣሣይ ነገር እዚያ ሲካሄድ ዝምታው ለእኛ የታወቀ ነው፡፡ „የፕሬዚዳንት ፑቲን ጭንቀት …የእሳቸውን ፍርሃቻ…“ - እነሱ እንደሚሉት- „…የሰሜን አትላንቲኩን የድፍረት ጉዞ….ይህን ሁሉ ተመልክተን፣የፕሬዚዳንቱን ችግር ለመረዳት ሙከራ እናደርጋለን…“ የሚሉ የአውሮፓና የጀርመን ፖለቲከኞች ቁጥር እዚህ  አሁንም ትንሽ አይደለም፡፡ በተቃራኒው እዚያ ሩሲያ ውስጥ „…ዛሬ እታሰራለሁ፣ነገ እገደላለሁ..“ እያሉ የዕለት ሥራቸውን በፍርሃትና በጭንቀት እዚያ የሚያካሄዱትን የጋዜጠኞች ሁኔታ „…ለመረዳት“ የእነሱንም ችግር „ለማየት“  እስከዚህም እነሱ አይጨነቁም፡፡ ብዙ ጋዜጠኞች እዚያ የማስፈራሪያና የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ደርሶአቸዋል፡፡ተይዘው የተደበደቡም አሉ፡፡ተገድለው የተጣሉም ጋዜጠኞች ቅጥር ትንሽ አይደለም፡፡

Mitarbeiterversammlung 2013 in Berlin Peter Limbourg

ፒተር ሊምቡርግ


ግን ደግሞ ደስ የሚለው አንዳንዴ ፣ እንደ አዲሱ የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር እንደ ሓይኮ ማስ ያሉ ሰዎች ከሌሎቹ የተለየ አቋም እነዚህ ፖለቲከኞች ሲያራምዱ ማየት ትልቅ ነገር ነው፡፡
ሌላዋ በዚህ የፕሬስ ነጻነት ቀን ስሙዋ አብሮ ዛሬ መነሳት ያለባት አገር ኢራን ናት፡፡ ኢራን ውስጥ እዚያ ፣ በአብዮት ጠባቂዎች ቁጥጥር ሥር ወድቀው በደልና ግፍ የሚፈጸምባቸው ጋዜጠኞች ቁጥር 23 እንደሆኑ ማንም ሰው ያውቃል፡፡ ግን ስለእነሱና በየጊዜው የዶቸ ቬለ ድምጽን ከሌሎቹ ራዲዮ ጣቢያዎች ጋር እንዳይሰራጩ መንግሥት እዚያ የሚያካሂደውን ተንኮል ፊት ለፊት ተነስተው የሚያጋልጡ ፖለቲከኞች እኛ እዚህ አላየንም፡፡እዚህም አልሰማንም፡፡
ከእሱ ይልቅ ጠቅላላውን የመካከለኛ ምሥራቅ አገሮችን ከሚያተራምሰውና እሥራኤልን ከምድረ-ገጽ አጠፋለሁ ብሎ ፣በየጊዜው  ከሚፎክረው መንግሥት ጋር ፣ አንድ ቀን ተቀራርበን አብረን እንሠራለን ብለው የሚያልሙ ፖለቲከኞች ቁጥር ትንሽ አይደለም፡፡ ሳውዲ አረቢያም አለች! እዚያ ጋዜጠኞች እየታሰሩ „…መኪና መንዳትን ለአንስታይ ጾታዎች እፈቅዳለሁ!...የሲኒማ ቤቶችን እከፍታለሁ!...“ ያሉትን አልጋ ወራሹን ብዙ ፖለቲከኞች እዚህ እንደ ትልቅ ተአምራተኛ ሰው ፣እሳቸውን ያደንቁአቸዋል፡፡
ግን „…ሓሳቤን በይፋ መግለጽ መብቴ ነው…“ ያለውን አሁን አለአግባብ እሥር ቤት ተወርውሮ እዚያ የሚማቅቀውን ወጣቱን ጸሓፊ ፣ራይፍ ባዳዊን አንድም ቀን ዞር ብሎ እሱን የሚያስታውሰው እዚህ የለም፡፡
የአፍሪካ አምባገነኖችም አሉ! የሕዝቦቻቸውን ሰበአዊ መበቶች ገፈው -በአፍሪካ ሥልጣኑን የነጠቁት አምባገነኖችም ፣ ጥዋት ማታ „…ገንዘብ አምጡ“ እያሉ እዚህ ከአውሮፓ መንግሥታት በየጊዜው ብዙ ብር ይሰበስባሉ፡፡ ለአገራቸው ብዙ መሥራት የሚፈልጉትን ወጣት ጋዜጠኞች ደግሞ እዚያ ሲያስሩ ዝም ብለው ያያሉ፡፡ የእርዳታ ገንዘብም ወጣቶቹ ለሥራቸው ማካሄጃ ሲጠይቁ እነሱን እዚህ ዞር ብሎ የሚያያቸው ሰው የለም፡፡ ዝርዝሩ ብዙ ነው፡፡


በእሲያ፣በባንግላዳሽና በፓኪስታን፣ በሶሪያና በሜክሲኮም ወይም እንደዚሁ በሌሎች አከባቢዎች የምናያቸው ሥዕሎች ከላይኞቹ ጋር አንድ የሆኑ፣የሚመሳሰሊም ናቸው! የቱርክ መንግሥት አለ፡፡ የፖላንድና የሓንጋሪም የሁለቱ መንግሥታት እርምጃም ለጋዜጠኞች ሕይወት  አመቺም አይደለም፡፡ ዕውነቱን ለመናገር ጊዜው በከንፈር መጠጣ ብቻ በቀላሉ የሚታለፍም አይደለም፡፡  የአውሮፓ መንግሥታት የጋዜጠኞች መብት ሲረገጥ እነሱ ከእንግዲህ ዝም ብለው ማየት የለባቸውም፡፡እኛም መራጩ ሕዝብ ፣ሥልጣን ላይ የወጡትን ፖለቲከኞች ፣የፕሬስ ነጻነት እንዲከበር እነሱን በየቀኑ ከመወትወት ወደኋላ  ማለት የለብንም፡፡
ከእንግዲህ „የልማትና የዕድገት ዕርዳታም“ ወደፊት ሲሰጥ „..ከሰበአዊ መበት መከበርና ከፕሬስ ነጻነት“ ጋር የግድ መያያዝ ይኖርበታል፡፡ በአምባገነኖች ጥጅካሬ ዲሞክራሲ በዓለም ዙሪያ አሁን እንደምናየው አደጋ ላይ ወድቃለች፡፡ መፍትሔ መድኃኒቱ ደግሞ የዲሞክራቶች አንድነት ነው፡፡ በዛሬው የዓለም የፕሬስ ቀን ጣቢያችን ዶቸ ቬለ የተቋቋመበትን 65 ኛውን አመቱን አብሮ ያከብራል፡፡ 
ጣቢያችን „ለፕሬስ ነጻነት በዓለም ዙሪያ“ የቆመ ድርጅት ነው፡፡ ይህንንም ቃላችንን ሳናጥፍ እንደ ጀመርነው ወደፊትም እንቀጥልበታለን!! ብሎ የቤቱ ሐተታ በዚህ ዓረፍተ ነገር መልዕክቱን ዘግቶአል፡፡
  

ፒተር ሊምቡርግ/ ይልማ ኃይለ ሚካኤል 

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች