1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፕረስ ነጻነት ይዞታ በፓኪስታን፣

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 13 2001

በዓለም ውስጥ የፕረስ ነጻነትን እጅግ ከሚጋፉትና ከሚከሰሱት አገሮች አንዷ ፓኪስታን መሆኗን RSF አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/HbZo
በእንግልት፣ ዛቻና በመሳሰለው አገሯን ለቃ ወደ ጀርመን የተሰደደችው ፓኪስታናዊቷ ጋዜጠኛ ፣ ሜራ ጀማል፣ምስል DW

ከ 173 አገሮች ፣ ፓኪስታን በፕረስ ነጻነት ገፋፊነት 152 ደረጃ ላይ ትገኛለች። በዓለም ውስጥ ፣ ከኢራቅ ቀጥላ፣ ለጋዜጠኞች ፀር የሆነች አገር ፓኪስታን ናት። በዚህ ዓመት ብቻ 3 ጋዜጠኞች በጥይት ተደብድበው ህይወታቸው አልፏል። አምና 7 ነበሩ። በተለይ፣ ስለሴቶች እኩልነትና ስለአክራሪ ሙስሊሞች የሚጽፉ፣ የሚናገሩ ጋዜጠኞች፣ ፍዳ ነው የሚያዩት። ሽብር ፈጠራው፣ ዛቻው፣ ክትትሉ፣ ያስጨነቃት አንዲት ፓኪስታናዊት ጋዜጠኛ ፣ ህይወቷን ለማትረፍ ጀርመን ከገባች በኋላ፣ ማብራሪያ ሰጥታለች።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል ዝርዝር ዘገባ አለው።

ይልማ ኃ/ሚካኤል፣

ተክሌ የኋላ፣