የፔጊዳ ሰልፍ መታገድ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 19.01.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የፔጊዳ ሰልፍ መታገድ

ፖሊስ ደርሶኛል ባለው መረጃ ምክንያት የድሬስደኑ ሰልፍ ቢገፋም በሌሎች የጀርመን ከተሞች ግን ፔጊዳ የጠራቸው ሰልፎች ይካሄዳሉ ።

ፔጊዳ የተባለው በአውሮፓ የእሥልምናን መስፋፋት እቃወማለሁ የሚለው ንቅናቄ ለዛሬ በምሥራቅ ጀርመንዋ በድሬስደን ከተማ ሊያካሂድ ያቀደው ሰልፍ መታገድ እዚህ ጀርመን እያነጋገረ ነው ። የፔጊዳ ሰልፍ ብቻ ሳይሆን በከተማይቱ ዛሬ ፔጊዳን በመቃወም ሊካሄድ የታሰበው የአደባባይ ሰልፍና ሌሎችም ህዝባዊ ስብሰባዎች መታገዳቸው ድጋፍም ተቃውሞም ገጥሞታል ። ፖሊስ ደርሶኛል ባለው መረጃ ምክንያት የድሬስደኑ ሰልፍ ቢገፋም በሌሎች የጀርመን ከተሞች ግን ፔጊዳ የጠራቸው ሰልፎች ይካሄዳሉ ። ስለ እገዳውና በእገዳው ላይ ስለሚሰነዘሩ አስተያየቶች የበርሊኑን ዘጋቢያችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን ኂሩት መለሰ በስልክ አነጋግራዋለች ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic