የፓን አፍሪቃ የንግድና ኢንዱስትሪ ጉባኤ | አፍሪቃ | DW | 29.11.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የፓን አፍሪቃ የንግድና ኢንዱስትሪ ጉባኤ

የአፍሪቃ ሃገራት የሚካሂዱት የንግድ ልዉዉጥ ከዉጭ ከሚያገኙት የእርዳታ ገንዘብ መጠን መብለጡ ተገለጸ።

አዲስ አበባ ላይ ለተካሄደዉና ዛሬ ለተጠናቀቀዉ የመላዉ አፍሪቃ የንግድ እና ባለኢንዱስትሪዎችምክር ቤት ጉባኤዉ ይህን ያመለከቱት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የእርስ በርስ ግብይቱ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባዉም አሳስበዋል። ጉባኤዉ የአፍሪቃ ሃገራት ምርቶቻቸዉን እንዴት አቀናብረዉ ወደዉጭ ቢልኩ ገቢያቸዉን ማጠናከር ይችላሉ በሚለዉ ላይም ተነጋግሯል። የንግድና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዝደንት ወ/ሮ ሙሉ ሰሎሞን ኢትዮጵያ ምርቶቿን ከአፍሪቃ ዉጭ ለመላክ ገበያ አለማጣቷን በማመልከት፤ የጥራት ደረጃን ጨምሮ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ግን መኖራቸዉን አመልክተዋል። ዘጋቢያችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል

ጌታቸዉ ተድላ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic