የፓናማ ሰነዶች እና ኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 13.05.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የፓናማ ሰነዶች እና ኢትዮጵያ

የፓናማ ዶሴዎች ወይም Panama Papers በመባል የሚታወቀዉ ዶሴ በዓለምአቀፉ የምርመራ ጋዜጠኞች «ICIJ» በኩል በተለያዩ አገራት ያሉ ባለስልጣናት እና ሌሎች ግለሰቦች ገንዘብ ማሸሻቸዉን የሚያሳዩ ምስጥራዊ ሰነዶች ይፋ ማድረግ ከጀመረ ሰንብተዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:13

የፓናማ ሰነዶች እና ኢትዮጵያ

በፓናማ የሚገኘዉ ሞሳክ ፎንሴካ የተባለዉ የሕግ አማካሪ ድርጅት የተለያዩ ሃገራት ባለስልጣናት እና ሌሎች ግለሰቦች ግብርን ለማጭበርበር እንዴት ድርጅቶቻቸን ከሃገራቸዉ ውጭ ማንቀሳቀስ እንደሚችሉና፣ በሙስና እንዲሁም በሌሎች ወንጀል ነክ ገንዘብን የያዙ ግለሰቦች እንዴት መሰወር እንደሚችሉ ምክር ይሰጣል በሚል መከሰሱ ይታወሳል።


ባለፈዉ ማክሰኞ የፓናማ ዶሴ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከሚንቀሳቀሱ ሁለት ኩባንያዎች ጋር ግንኙነት እንዳለዉ ይፋ ሆንዋል። እነዚህ ኩባንያዎች የመጀመርያዉ «ፖሊ ኢትዮጵያ ፔትሮሊዬም» የተሰኘዉ የቻይና ኩባኒያ በሃገሪቱ በነዳጅና ጋዝ ፍለጋ የተሰማራ መሆኑን ይፋ የሆነዉ ዶሴ ያሳያል። ሁለተኛዉ ባለቤቱ ማን እንደሆነ ያልታወቀዉ «ግርማ አግሪካልቼር» ኩባንያ ሲሆን በኢትዮጲያ ሕጋዊ አካል ኖሮት እንደሚንቀሳቀስ ዶሴዉ ያስረዳል።

Karte Äthiopien englisch


ይፋ በሆነዉ ዘገባ ላይ መረጃዎቹ የተሟሉ አይደሉም፣ ለምሳሌ ስም አልያም አድራሽዎች ብቻ የተመለከቱበት ሰነድ በመሆኑ ኩባንያዎቹ ዘረፋን ፈፅመዋል ወይም ወንጀል ስርተዋል ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር አይቻል ሲሉ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት ጋዜጠኛ አርጋዉ አሽኔ ይገልፃሉ። እንድያም ሆኖ መረጃዉ ለጥርጣሪ ጋባዥ መሆኑን ጋዜጠኛ አርጋዉ ገልፀዋል። ከኢትዮጵያ ጋር የተቆራኙት እነዚህ ሁለት ኩባኒያዎች ብቻ ሳይሆኑ በጥርጣሪ ዓይን የሚታዩት በማዕድን ፍለጋ የተሰማሩ በጣሊያኖች እና በእስራኤላዉያን የጋራ ትብብር የሚንቀሳቀሱ እንዳሉም ጋዜጠኛ አርጋዉ ገልፀዋል።


ፓናማ ዶሴ በርካታ ድርጅቶችና ግለሰቦች እንዳሉ የተናገሩት ጋዜጠኛ አርጋዉ አለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያ ዉስጥ ይህን ጎልጉሎ የሚያወጣ ጠንካራ የመገናኛ ብዙኃንና ገንዘብ ባለመኖሩ ሊዳፈን ችሎአል። የኢትዮጵያ የፋይናንስ ቁጥጥር ሁኔታ ደካማ መሆኑ ለእንደዚህ አይነት ክስተት በር ይከፍታል ያሉት ጋዜጠኛ አርጋዉ አገሪቱ ዉስጥ የሚታየዉን የገንዘብ ማሸሽ ጉዳይ በዛም አስከፊ መሆኑን ይናገራሉ።


ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚታየዉ የመረጃ አያያዝና አመዘጋገብ ልምድ ከዛም አልፎ መረጃ ለህዝብ ይፋ የማድረግ ልምዱ ስለሌለ እንድህ ዓይነት ክስተቶችን ለመከታተል አስቸጋሪ መሆኑን ተናግረዋል።

መርጋ ዮናስ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic