የፓርቲዎች የክርክር መድረክና የሰማያዊ ፓርቲ ስሞታ | ኢትዮጵያ | DW | 27.03.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የፓርቲዎች የክርክር መድረክና የሰማያዊ ፓርቲ ስሞታ

ዛሬ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በተካሄደዉ የፓርቲዎች ክርክር ሰማያዊ ፓርቲ እንዳልሳተፍ ተደረኩ ሲል አማረረ። የኢትዮጵያ ብሮድካስቲግ ኮርፖሬሽን በበኩሉ የክርክር መድረኮቹ በእጣ መደልደላቸዉን ገልጾአል።ይህ የተደረገዉም በመጭዉ እሁድ አዲስ አበባን ጨምሮ በ 15 የተለያዩ ከተሞች ለተጠራዉ ሰላማዊ ሰልፍ ሆን ተብሎ ለመጉዳት ነዉ ሲሉ፤ የፓርቲዉ ሊቀመንበር ኢንጂኔር ይልቃል ጌትነት ለዶይቼ ቬለ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ብሮድካስቲግ ኮርፖሬሽን በበኩሉ የክርክር መድረኮቹ በእጣ መደልደላቸዉን፤ ሰማያዊ ፓርቲ ግን በሰብዓዊ መብቶችና ዲሞክራሲ ላይ በተካሄደዉ ዉይይት አለምደባዉ መሳተፍ አለብኝ ብሎ ከሌላ ፓርቲ ጋር በመቀየሩ፤ ዛሬ ሊሳተፍ አለመቻሉን ገልፆአል። ይህንንም ከሰማያዊ ሰልፍ ጋር አያይዞ ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀምም ተገቢ አይደለም ሲሉ የድርጅቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ተሻለ በቀለ መልስ ሰጥተዋል።


ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር


አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic