የፓርላማ ተወካዮች ዉይይት በአዋጁ ላይ | ኢትዮጵያ | DW | 01.03.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የፓርላማ ተወካዮች ዉይይት በአዋጁ ላይ

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሁለተኛ ጊዜ የተደነገገዉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማፅደቅ ለነገ አርብ ለአስቸኳይ ስብሰባ ተጠርቷል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:46

አነጋጋርዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ

አዋጁ ላይ ዉሳኔ ለመስጠት እንዲበጅ የምክር ቤቱ አባላት ከትናንት ጀምሮ በየወከሉት ክልል መሠረት ለየብቻቸዉ ዉይይት ማድረጋቸዉን ለመንግስት ቅርበት ያላቸዉ ምንጮች ይገልፃሉ። ምንጮቹ እንደሚሉት «የኦህዲድ የፓርላማ አባላት ሙሉ በሙሉ» አዋጁን እንደተቃወሙትና ለዛሬ ሌላ የዉይይት ቀጠሮ መያዛቸዉን ነዉ።

የፖለትካ ተንታኝ አቶ ደረጀ ገረፋ ቱሉ በትላንትናዉ እለት አራቱም የኢሕአዴግ አባል ድርጅትቶች ማለትም የህወሓት፣ የደኢህዲን፣ የብአዴን እንዲሁም የኦህዲድ  የፓርላማ አባላት በዚህ ዉይይት ላይ መሳተፋቸዉን በፌስቡክ ገጻቸዉ ላይ አካፍለዋል። «የደኢህዲን እና የህወሃት  አባላት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈላጊነት ላይ ሲስማሙ፤ የኦህዲድ የፓርላማ አባላት ግን ሙሉ በሙሉ ተቃውመው ወጥተዋል፤ የብአዴን ግን በግልፅ አልታወቀም» ሲሉም አክሎበታል። አቶ ደረጀ ከለጠፉት ከጥቅት ሰዓታት በዋላ በኦሮምያ ዩኒቬርስቲ የአካዳምክ አማካሪ  ዶክተር ሚሊኬሳ ሚዳጋም በትላንትናዉ እለት የኦህዲድ የፓርላማ አባላቶች አዋጁ ልፈፀም አይገባም የምል አቋም ይዞ እንደተለያዩ በፌስቡክ ገፃቸዉ ላይ አስፍረዋል።

አቶ አወሉ አብዲ በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን ቦቆጅን ነዉ፤ የሚወክሉት፤ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ሶማሊያና ከኦሮሚያ አዋሳኝ ድንበር የተፈናቀሉትን ስራ ለማስያዝ በሐራር ከተማ ቢገኙም ስብሰባዉ ትላንት መካሄዱን አረጋግጠዋል። ከዚህ በፊት አዋጁ ተደንግጎ እንደነበረ የጠቀሰሱት አቶ አወሉ ጥንካሬዉና ግድፈቱ ምን እንደነበረ ሊጠና ይገባል፣ አሁን ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ለምን ታወጀ፣ የኢሕአዴግ የስራ አስፈጻሚ የሕዝቡን ጥያቄ ለምን አለመለሰም የሚሉትም መታየት አለበት ይላሉ።

አቶ አወሉ፣ «ለኔ አዋጅ ታወጀ፣ አልታወጀ የኦሮሞን ብሎም የኢትዮጵያ ህዝብን የሚጎዳ አይፈፀምም። አንዳንዴ አሳሳቢ የሚሆነዉ፣ የአገርቱን ሰላም የማስጠበቅ አስፈላጊነት ነዉ። ግን እንደኔ ሰላም በጦር ሃይል ይጠበቃል የሚል እምነት የለኝም። ሕዝብን መስማት፣ አብሮ መወያያት፣ ለሕዝቡ ጥያቄ መልስ መስጠት መሆን አለበት እንጅ ይቺ አገር ሰላሟ በጦር ተከብሮ አያዉቅም፣ ቢከበርም ቀጣይነት የለዉም። እንደ አንድ ሰዉ በዝህ መንገድ ነዉ የምረዳዉ።»

ኦሮሚያን ወክሎ ትላንት የተወያዩት አዋጁን ዉድቅ አደረጉ ቢባልም፣ ዳግም ለመወያየት ለዛሬ ቀጠሮ እንዳላቸዉም አቶ ደረጀና ዶክተር ሚሊኬሳ በፅሁፋቸዉ አመልክተዋል።ዶክተር ሚኬሳ የፓርላማ አባላቶች ተጠያቂነታቸዉ ለህሊናቸው፣ ለሕዝባቸው እና ለህገ-መንግስታቸው መሆኑን አክሎበታል።

የሕግ ባለሙያዉ አቶ ተማም አባቡሊጉ ዶክተር ሚሊኬሳ በመጨረሻ ከጠቀሱት ጋር ይሳማማሉ። አቶ ተማም እንደሚሉት የፓርላማ አባላት የሕዝብ ተወካይ እንደመሆናቸዉ መጠን የመረጣቸዉ ህዝብ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንዳታፀድቁ ወይም አፅድቁ የማለት ሕገ-መንግስታዊ መብት አለዉ ይላሉ። የፓርላማ አባላት በመንግስት ፍላጎትና በሕዝቡ ጥያቄ መካከል መያዛቸዉን የህግ ባለሙያዉ አቶ ታማም ይናገራሉ።

የዶይቼ ቬሌ የፌስቡክ ተከታታዮችም የተለያዩ አስተያቶችን ሰጥተዋል። አሼ ዘክን የተባሉት ግለሰብ «ሀገር ለማረጋጋት ሲባል እንዲሁም መንግሥት ያሰበውን ለውጥ ለህዝብ እንዲያሳይ ጊዜ ሊኖረው ይገባል፣ አዋጁን መቃወም ፋይዳው አልታየኝም» ሲል ግዛቸዉ አሰፋ ደግሞ «የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በነፃ ምርጫ ተመርጠው ባይወከሉም የህዝብ ብሶት ሰምተው ይህን አዋጅ ውድቅ ካደረጉት መልካም ነገር እንደሰሩ ታሪክ ይመዘግብላቸዋል፣» ብለዋል። ሙሉ ዘገባዉን ለማዳመጥ ከላይ ያለዉን የድምፅ ዘገባ ይጫኑ።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic