የፓለቲካ ውጥረት በፑንትላንድ | ኢትዮጵያ | DW | 21.08.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የፓለቲካ ውጥረት በፑንትላንድ

ከሶማሊያ ጋር ስትወዳደር አንፃራዊ ሰላም ያላት የሰሜን ሶማሊያዋ የፑንትላንድ አስተዳደር ከፍተኛ የደህንነትና የፖለቲካ ውጥረት እንደሰፈነባት አንድ ዓለም ዓቀፍ ድርጅት አስታወቀ ።

የግጭቶችን መንስኤ የሚያጥናውና መፍትሄያቸውንም የሚጠቁመው ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ የተባለው ቡድን እንዳስታወቀው የፑንትላንድ ውስጣዊ ችግር በአፋጣኝ ካልተፈታ መዘዙ ከፑንትላንድ አልፎ ለአፍሪቃ ቀንድም ይተርፋል ። ከክራይስ ግሩፕ ጆን ግሪንዋልድ ለዶይቼቬለ የአማርኛው ክፍል እንደተናገሩት የፑንትላንድ ችግሮች ባለሉበት ከተተዉ የሀገሪቱ መዋቅሮች ይፈራርሳሉ ፤ የአፍሪቃ ቀንድም ለባሰ ውጥረት ይዳረጋል ። ጆን ግሪንዋልድን ያነጋገረው አበበ ፈለቀ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል ።

አበበ ፈለቀ :ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ