የፑቲን የጀርመን ጉብኝት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 01.06.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የፑቲን የጀርመን ጉብኝት

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዛሬ ወደ ጀርመን ተጉዘው በርሊን ላይ ከጀርመን መህራይተ መንግስት አንጌላ መርክል ጋ ተወያይተዋል ።

ፑቲን ለሶስተኛ ጊዜ በፕሬዝዳንትነት ከተመረጡ በኃላ ጀርመንን ሲጎበኙ የዛሬው የመጀመሪያ መሆኑ ነው ።ስለ ጉብኝታቸው አለማ እና ስለ ሁለቱ ሃገሮች ግንኝነት ከበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል ጋ የተደረገ ቃለመጠይቅን ማድመጥ ይቻላል።

በሩሲያ ዳግም የፕሬዝደንትነቱን ስልጣን የጨበጡት ቪላድሚር ፑቲን ዛሬ ለጉብኝት ጀርመን በርሊን ገብተዋል። በወታደራዊ ክብር እንግዳቸዉን በፅህፈት ቤታቸዉ የተቀበሉት መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ከፑቲን ጋ ከሐገሮቻቸዉ ግንኙነት በተጨማሪ የሶርያን ቀዉስ በማንሳት መወያየታቸዉ ተገልጿል። ሜርክል ሳለነሷቸዉ ነጥቦች ሲገልፁ ይህን ብለዋል፤
«የሶርያ ህዝብ ስለሚገኝበት ሁኔታ ያለን ግንዛቤ ተመሳሳይ ነዉ። በአሁኑ ወቅት እዚያ ያለዉ ሁኔታ አስከፊ ነዉ። እኔ ለማለት የምችለዉ ያቺ አገር ወደእርስበር ጦርነት እንድትገባ ማንም አይፈልግም፤ ሆኖም የእርስ በርስ ጦርነቱ እንዳይከሰት መደረግ የሚገባዉ ጥረት ሁሉ መከናወን አለበት። ለዚህም እያንዳንዱ የየበኩሉን አስተዋፆኦ ማድረግ ይኖርበታል። የፖለቲካ መፍትሄን እንደግፋለን፤ በዚህ ነጥብ ላይ ነዉ የተወያየነዉ።»


የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዶ ቬስተር ቬለ ሩሲያ ከሶርያ ጋ ያላትን ስልታዊ ግንኙነት ስለማይጎዳ አመፁን ለማስቆም የሚደረገዉን ጥረት እንድታስተዉለዉ አሳስበዋል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል ደግሞ ሩሲያ ለሶርያ መሳሪያ ማረቧን ባስቸኳይ እንዲያስቆሙ ፑቲንን ጠይቋል። ፑቲን በበኩላቸዉ ወደእርስበርስ ጦርነት የሚያመራን ወገን ሐገራቸዉ እንደማትደግፍ በመግለፅ ከመራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋ በዚህ ረገድ እንደሚስማሙ ነዉ ያመለከቱት፤
«ሩሲያ የትኛዉንም አገዛዝ ትደግፋለች እያሉ ለሚናገሩ በዚህ ጉዳይ ፕሬዝደንት አሳድን ማለት ነዉ የአንድ ወገን ድጋፍ ትሰጣለች የሚባለዉ ስህተት ነዉ። ከሶርያ ጋ የረዥም ጊዜ ግንኙነት ነዉ ያለን። የእርስ በርስ ጦርነት እንዳይከተልም የሚጋጩትን ወገኖች አንደግፍም በዚህ ረገድ ከመራሂተ መንግስቷ ጋ እስማማለሁ። የጋራ ሃላፊነታችን ይህን የማይፈለግ ሁናቴ መግታት ነዉ። ዛሬ ወደእርስበር ጦርነት የሚያስገቡ ሁኔታዎችን ተመልክተናል፤ ይህ በጣም አደገኛ ነዉ።»
ፑቲን ከጀርመን ቆይታቸዉ በኋላ ወደፓሪስ በማቅናት ከአዲሱ የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ፍራንሷ ኦሎንድ ጋም እንደሚነጋገሩ ይጠበቃል።

ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic