የፎልክስ ቫገን ፍላጎት በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 29.01.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የፎልክስ ቫገን ፍላጎት በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የጀርመን ፕሬዝደንት ፍራንክ-ቫልተር ሽታይማር በተገኙበት ሥነ-ሥርዓት ላይ፣ ሥምምነቱን የፈረሙት በከሠሐራ በታች በሚገኙ የአፍሪቃ ሐገራት የኩባንያዉ ኃላፊ ቶማስ ሼፈርና የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር አበባ አበበያሁ ናቸዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:11

የጀርመኑ ግዙፍ የአዉቶቢል አምራች ኩባንያ ፍላጎት በኢትዮጵያ

የጀርመኑ ግዙፍ አዉቶሞቢል  አምራች ኩባንያ  ፎልክስ ቫገን (VW-በጀርመንኛ ምሕፃሩ) ኢትዮጵያ ዉስጥ የመኪና መገጣጠሚያና መለዋወጪያን ጨምሮ  የመኪና ቁሳቁሶች ማምረቻና መሸጫ ማዕከላትን መክፈት የሚያስችለዉን የመግባባያ ሰነድ ከኢትዮጵያ የኢንቨስትመት ኮሚሽን ጋር ተፈራረመ።ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የጀርመን ፕሬዝደንት ፍራንክ-ቫልተር ሽታይማር በተገኙበት ሥነ-ሥርዓት ላይ፣ ሥምምነቱን የፈረሙት በከሠሐራ በታች በሚገኙ የአፍሪቃ ሐገራት የኩባንያዉ ኃላፊ ቶማስ ሼፈርና የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር አበባ አበበያሁ ናቸዉ።ግዙፉ የአዉቶሞቢል አምራች ኩባንያ በስምምነቱ መሠረት ኢትዮጵያ ዉስጥ መወረት ሲጀምር ለኢትዮጵያዉያን የሥራ ዕድል ይፈጥራል፣ ለሐገሪቱ የዉጪ ገበያ ዕድል ይከፍታልም ተብሏል።

ጌታቸዉ ተድላ የኃይለጊዮርጊስ 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic