የፎልክስ ቫገን የመኪና ኩባንያ ቅሌት | ዓለም | DW | 22.09.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የፎልክስ ቫገን የመኪና ኩባንያ ቅሌት

ፎልክስ ቫገን የመኪና አምራች ኩባንያ በፎልክስ ቫገንና አዉዲ የንግድ ምልክት ስር የሚያቀርባቸዉ በናፍጣ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎቹ ከዩኤስ አሜሪካ ገበያ ታገዱ። ኩባንያዉ ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ በሸጣቸዉ በሚሊዮን በሚቆጠሩ የናፍጣ መኪኖች ላይ የተጭበረበረ የብክለት መቆጣጠሪያ በመግጠሙ ክስ እንደሚመሠርትበት የአሜሪካ የፍትሕ ሚኒስቴር አስታዉቋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:35
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:35 ደቂቃ

የፎልክስ ቫገን ኩባንያ የማጭበር ቅሌት


ይህ ውሳኔ የተወሰደው የዩኤስ አሜሪካ የተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ መስሪያ ቤት ፎልክስ ቫገን የመኪና አምራች ኩባንያ ለገበያ የቀረቡት ተሽከርካሪዎች የሚተፉትን ከባቢ አየርን የሚጎዳውን የጢስ መጠን በሶፍትዌር አማካኝነት ዝቅ የማድረግ የማጭበርበር ተግባር ፈጽሞዋል ሲል ካጋለጠ በኋላ ነው። ኩባንያዉም ስህተት መስራቱን አምኖ ይቅርታ ጠይቋል። የዩኤስ አሜሪካ የከባቢ ጥበቃ ጉዳይ ባለስልጣን መስርያ ቤት ይፋ እንዳደረገዉ ፎልክስ ቫገን የተሽከርካሪ ኩባንያ 482 ሺህ ተሽከርካሪዎችን በማጭበርበር ለገበያ አቅርቦአል። በሌላ በኩል ድርጅቱ በዓለም ዙርያ 11 ሚሊዮን በዚሁ መልክ በናፍጣ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ኩባንያዉ ማቅረቡ ነዉ የተመለከተዉ። ዬኤስ አሜሪካ ፎልክስ ቫገን የመኪና አምራች ኩባንያ ላይ የጣለችዉን እገዳ ተከትሎ ፈረንሳይ ኢጣልያ ብሪታንያ ስዊጠርላንድ ደቡብ ኮርያ እና አዉስትራልያ ነገሩ በፍጥነት እንዲጣራ ጠይቀዋል። የዩኤስ አሜሪካዉ ዘጋብያችን አጠር ያለ ዘገባ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic