የፍትህ ሥርዓቱ ሀገርኛ ሚና | ኢትዮጵያ | DW | 12.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የፍትህ ሥርዓቱ ሀገርኛ ሚና

ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ ክልሎች የሚቀሰቀሰው ግጭት ዛሬም አልረገበም። በአፋር እና ሶማሌ ብሄረሰቦች ፣ በጋሞ፣ በኦሮሚያ ፣ በመስቃንና ማረቆ፣ በስልጤ አካባቢ የተነሱት ግጭቶችን በባህላዊ ስርዓት ለመፍታት ጥረት መደረጉ  ይታወቃል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:35

መንግስት ለግጭቶች እልባት የመስጠቱ ጉዳይ እምብዛም ነው

በአስተዳደር እና ወሰን አከላለል እና በሌሎች ምክንያቶች የሚቀሰቀሱ ግጭቶች በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት እየደረሱ ነዉ። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል። መንግስት በክልሎች በሚቀሰቀሱ ግጭቶች እልባት የመስጠቱ ጉዳይ እምብዛም ነው ሲባል ይደመጣል። እነዚህ ግጭቶች ወዴት እያመሩ እንደሆነ በግልፅ የሚታወቅ ነገር የለም። ይሁንና ከዚህ ቀደም የሀገር ሽማግሌዎች አንዳንድ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረውን ግጭት በመፍታት ዘላቂ እርቀ ሠላም ለማውረድ ችለዋል። የሀገር ሽማግሌዎቹ ለረጅም ዘመናት የዘለቀው ታሪካዊ ትስስር፣ አንድነትና ወንድማማችነት በህዝቦች መሀል እንዲጠነክር የአስታራቂነት ድርሻቸውን እንደተወጡ የብዙዎች እምነት ነው፡፡ በሀይማኖታዊና ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓት ግን ችግሮቹ እየተፈቱ እንደሆነ ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ በአዲስ አበባ ዩኒበርስቲ ሶሻል አንትሮፖሎጂ ረዳት ፕሮፌሰር ይናገራሉ። «ግጭቱ የለውጡን ስርዓት ተከትሎ እዚህም እዛም ፈንድተዋል። መሠረታዊ የሆኑ የግጭት አፈታት ስርዓቶች አሉ። የፍትህ ስርዓት ግጭት አፈታት አንደኛው ነው፤ ሁለተኛው ሀይማኖታዊ እንደዚሁም ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓቶች ናቸው። የመንግሥት የፍትህ ስርዓት አሁን የተፈጠሩትን ግጭቶች የመፍታት አቅም አለው ብዬ አላምንም። ተጨባጭ ነገር እያየን ያለነው የባህላዊና ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ስርዓቶች በተለያየ ደረጃ ጣልቃ በመግባት ጉዳዩን በሚገርም ሁኔታ እየፈቱ እንዳሉ ነው።»

ከመንግሥታዊ የፍትህ ስርዓት፣ ባህላዊውና ሀይማኖታዊ የሆነው የሀገር ሽማግሌዎች ችግርን የመፍታቱ ሚና የተሻለ እንደሆነ ዶ/ር ከይረዲን ያስረግጣሉ።  «ሽማግሌዎች የገቡባቸው ዕርቅ ባህላዊ ህግጋት የተደገፉ ስለሆኑ ለችግሩ እልባት የመፍጠራቸው አቅም በየትኛውም ደረጃ ሲመዘን ከመንግሥታዊ ፍትህ ስርዓት የተሻሉ ናቸው። ለምሳሌ፦ አባ ገዳዎች በቅርቡ በኦፒዲ አመራሮችና በኦነግ መካከል ያደረጉት የዕርቅ ሥነ ሥርዓት እስካሁን ድረስ ሲመረቅዝ አላየንም።» የበለጠ ተጠንተው የፍትህ ሥርዓት ውስጥ መካተት ቢችል ግጭት ከመፍታት አልፎ ሰላም በመፍጠር ወደፊትም የበለጠ ሚና ይኖራቸዋልም ብለዋል። ሀጂ ገዳ ሙርከቶ አባገዳና የሀገር ሽማግሌ ናቸው። በኦሮሚያ ምስራቅ ሸዋ ዞን ነው የሚኖሩት። እሳቸውም እንዲሁ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ይናገራሉ። ግጭቶች በዚሁ ከቀጠሉ መቆጣጠር ከምንችለው በላይ ሊሆን እንደሚችልም፤ ካሁኑም እልባት ሊበጅለት ይገባል ካልሆነ የሀገርን ሰላም ማምጣት አንችልም ብዙዎች ሲሉ ይደመጣል።

ነጃት ኢብራሂም

ነጋሽ መሐመድ  

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች