የፍሲካ በአል አከባበር በጀርመን | ባህል | DW | 24.03.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የፍሲካ በአል አከባበር በጀርመን

በአገራችን በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ የፋሶካ ጾም ከጀመረ ሶስተኛ ሳምንቱ አልቆ ወደ አራተኛዉ በመዝለቅ ላይ ነዉ። በአለማችን የሚገኙ የካቶሊክ እና የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮች ደግሞ የትንሳኤን በአል በማክበር ይገኛሉ። ጀርመናዉያንም ትንሳኤ ዛሪ 23.03.08 በማክበር ላይ ናቸዉ። ታድያ በጀርመናዉያን ዘንድ የትንሳኤን በአል እንዴት ይከበራል?

ለፋሲካ በቀለም ያሸበረቀዉ ቅቅል እንቁላል

ለፋሲካ በቀለም ያሸበረቀዉ ቅቅል እንቁላል

በአለማችን የሚገኙ የካቶሊክ እና የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ዛሪ ትንሳኤን በአል በማክበር ላይ ይገኛሉ። በጀርመንም በአለፈዉ አርብ የስቅለት ቀን መታሰብያን እንዲሁም እሁድ እና ሰኞን የትንሳኤን በአል በማስመልከት የመንግስት መስሪያ ቤቶች ትምህርት ቤቶች እና ድርጅቶች ዝግ ናቸዉ። በጀርመን የፋሲካ በአል ሲታወስ በቀለም ያሸበረቀ የእንቁላል ቅቅል፣ እንዲሁም ከተለያዩ ነገሮች የተሰራ የጥንቸል ምስል በጠረቤዛ መቀመጡ ከ 17 ምዕተአመት ጀምሮ የመጣ ባህላዊ ልማድ መሆኑን ጽሁፎች ያስረዳሉ።
ባገራችን የፋሲካ በአልን ስናከብር ብንችል በግ አርደን ካልሆነም ቅርጫ ስጋ በማህበር ገዝተን አልያም ቢያንስ ቢያንስ ዶሮ አርደን ዳቦ ጋግረን ቄጠማ ጎዝጉዘን እንደምናከብረዉ ሁሉ በጀርመናዉያን ቤትም በየትራስ እና ሶፋዉ ስር ወይም በበር ጥግ እንዲያዉ እቤት በተገኘዉ መደበቅያ ስፍራ ሁሉ በቀለም ያሸበረቀ የእንቁላል ቅቅል ይደበቃል። በጠረቤዛዉ ላይ በጥንቸል ምስል የተጋገረ ብስኩት ወይም ከቸኮላታ የተሰራ እንቁላል ቅርጽ ያለዉ ምስል ወይም ጥንቸል ምስል በምግብ ጠረቤዛ ላይ ይገኛል። በአሉ በተለይ ለህጻናት በመሆኑ ጥንቸልዋ አስቀምጣዉ እንደሄደች በተለያየ ቀለም ያሸበረቀዉ የእንቁላል ቅቅል በተለይ ህጻናት ፈልገዉ እንዲያገኙ ነዉ። በነገራችን ላይ እዚህ ላይ ህጻናቱ እንቁላሉን አስቀምጣ የሄደችዉ ጥንቸሏ መሆንዋን ያምናሉ። የፋሲካ እለት ይህንኑ እንቁላል ለፍለጋ ሲነሱ ጥንቸሏ አስቀምጣዉ የሄደችዉን እንቁላል እንፈልግ ሲሉ ነዉ የሚነሱት። ስለ ጀርመናዉያኑ የፋሲካ በአል አከባበር ያጠናቀርነዉን ያድምጡ