የፍርድ ቤት ዉሳኔ አፈፃፀም መዘግየት እንደ የሕግ የበላይነት ፈተና  | ኢትዮጵያ | DW | 22.01.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የፍርድ ቤት ዉሳኔ አፈፃፀም መዘግየት እንደ የሕግ የበላይነት ፈተና 

የፍርድ ቤት ዉሳኔ አፈፃፀም መዘግየት የሕግ የበላይነትን ፈተና ዉስጥ እያስገባ መምጣቱን የሕግ ባለሞያ እና ፖለቲከኞች አመለከቱ። ፍርድ ቤት በዋስትና የሚያሰናብታቸውን ተጠርጣሪዎች ፖሊስ  ያለ በቂ ማስረጃ ያስራል የሚሉ ቅሬታዎች ከተከሳሾች እና ጠበቆቻቸው በተደጋጋሚ ይሰማል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:59

ተጠርጣሪዎችን ፖሊስ  ያለ በቂ ማስረጃ ያስራል የሚሉ ቅሬታዎች ይሰማሉ

የፍርድ ቤት ዉሳኔ አፈፃፀም መዘግየት የሕግ የበላይነትን ፈተና ዉስጥ እያስገባ መምጣቱን የሕግ ባለሞያ እና ፖለቲከኞች አመለከቱ። ፍርድ ቤት በዋስትና የሚያሰናብታቸውን ተጠርጣሪዎች ፖሊስ  ያለ በቂ ማስረጃ ያስራል የሚሉ ቅሬታዎች ከተከሳሾች እና ጠበቆቻቸው በተደጋጋሚ ይሰማል። የሕግ ጠበቃ ከድር ቡሎ፦ ረቡዕ ዕለት ከገላን ማረሚያ ቤት የተለቀቁት ደንበኞቻቸው ወጣት ኦብሳ አብዲሳ እና አብዱልገፋር ኡማር በፍርድ ቤት በዋስ የመለቀቅ መብት ከተጠበቀላቸው ውሎ አድሯል ብለዋል። ከትናንት በስትያ በአንደኛዉ ክሳቸው ነፃ የተባሉት አቶ ልደቱ አያለው የተከሰሱበት ሂደት ፖሊቲካዊ ነበር ያሉት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰረዘው ኢ. ዴ. ፓ. ፓርቲን ፕሬዝደንት አቶ አዳነህ ታደስ ናቸው። በገዥው ፓርቲ በኩል አስተያየት የሰጡን በብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ተቋማት ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ዓለሙ ስሜ በበኩላቸው መንግስት እና ፓርቲያቸው በፍትህ ተቋማቱ ሥራ ጣልቃ አይገባም ብለዋል። 
ሥዩም ጌቱ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሠ
 

Audios and videos on the topic