የፍርድ ቤት ዉሎ | ኢትዮጵያ | DW | 07.06.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የፍርድ ቤት ዉሎ

የባለ ራዕይ ወጣቶች ማኅበር ጊዜያዊ አመቻች ኮሚቴ ምክትል ፕሬዝደንት እና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድ በዋስ እንዲለቀቅ ፍርድ ቤት ዛሬ ወሰነ።

ላለፉት 15 ቀናት በእስር የቆየዉ ወጣት ብርሃኑ በአምስት ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቅ ነዉ የአዲስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የወሰነዉ። ወጣቱ መጀመሪያ ሰማያዊ ፓርቲ ያዘጋጀዉን ሰላማዊ ሰልፍ ታስተባብራለህ የሚል ምርመራ እንደተካሄደበት እና ኋላም ለግንቦት ሰባት ቅስቀሳ ታካሂዳለህ የሚል ምርመራ ይካሄድበት እንደነበር የማኅበሩ ፕሬዝደንት ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። በሌላ የፍርድ ቤት ዜና ደግሞ የጥንታዊ ኢትዮጵያ ጀግኖች ማኅበር ፕሬዝደንትና ሌሎች ሁለት የአመራር አባላት በማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረዉ ፍርድ ቤት ከቀረቡ በኋላ በዋስ ተለቀዋል። ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ከአዲስ አበባ ዘገባ ልኮልናል

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic