የፍልስጤም ጊዜያዊ መንግሥትና እስራኤል | ዓለም | DW | 03.06.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የፍልስጤም ጊዜያዊ መንግሥትና እስራኤል

የፍልስጤም ራስ ገዝ መስተዳድር ጊዜያዊ ተጣማሪ መንግሥት መመስረቱ ትናንት ይፋ ከሆነ በኋላ በዮናይትድ ስቴትስ እና በእስራኤል መካከል ከፍተኛ የአመለካከት ልዩነት ተፈጥሯል።

በርካታ የእስራኤል ሚኒስትሮች ዛሬ ዮናይትድ ስቴትስን ከአዲሱ የፊልስጤም መንግሥት ጋር ተባብራ ለመስራት ማቀዷን ሲተቹ ነው የዋሉት። ዮናይትድ ስቴትስ አዲሱ ጥምር መንግሥት ይፋ እንደሆነ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ሀገሪቱ ከፍልስጤም ራስ ገዝ አስተዳደር ጋር ያላትን ትብብር ጠብቃ እንደምትቆይ እና የርዳታ ገንዘብ መስጠቷን እንደምትቀጥል አስታውቃ ነበር። አዲሱን የፍልስጤም ጊዜያዊ ጥምር መንግሥት አስመልክቶ እስራኤል ሥለያዘችዉ አቋም-ሀይፋ የሚገኘው ወኪላችን ግርማው አሻግሬ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።

ግርማው አሻግሬ

ልደት አበበ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic