የፍልስጤም ለጋሽ ሐገራት ጉባኤ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 01.02.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የፍልስጤም ለጋሽ ሐገራት ጉባኤ

ትናንት አካባቢዉን የጎበኙት የጀርመኑ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ዚግማር ጋብርኤል እንዳሉት የእስራኤል መሪዎች የሁለት መንግሥታት መፍትሔ ከሚለዉ መርሕ ለመራቅ ማቅማማታቸዉ አዉሮጶችን እያሳሰበ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:34

እስራኤል ከ2 መንግሥታት መርህ መራቋ አዉሮጶችን አሳስቧል

እስራኤል ከዚሕ ቀደም ከፍልስጤሞች ጋር ባደረገችዉ ዉል መሠረት ከፍልስጤም ጋር ሁለት መንግሥታት ለመመሥረት እንድትደራደር የአዉሮጳ ዲፕሎማቶች እና ፖለቲከኞች እያሳሰቡ ነዉ። ትናንት አካባቢዉን የጎበኙት የጀርመኑ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ዚግማር ጋብርኤል እንዳሉት የእስራኤል መሪዎች የሁለት መንግሥታት መፍትሔ ከሚለዉ መርሕ ለመራቅ ማቅማማታቸዉ አዉሮጶችን እያሳሰበ ነዉ። ብራስልስ ተሰብሰበዉ የነበሩት የፍልስጤም ለጋሽ ሐገራት ተወካዮችም የፍልስጤም እና የእስራኤልን ዉዝግብ ለማስወገድ አብነቱ የሁለት መንግሥታት «ድርድር ነዉ» ብለዋል። የአዉሮጳ ፖለቲከኞች እና ዲፕሎማቶች መልዕክት የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አወዛጋቢዋን የእየሩሳሌም ከተማን የእስራኤል ዋና ከተማ እንደሆነች እዉቅና መስጠታቸዉን በቀጥታ የሚቃረን ነዉ። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ያጠናቀረውን ዝርዝር ዘገባ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic