የፍልስጤምና የእስራኤል ግጭት | ዓለም | DW | 13.10.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የፍልስጤምና የእስራኤል ግጭት

ፍልስጤማዉያን ወጣቶች በእስራኤል ፀጥታ አስከባሪዎች ላይ ድጋይ መወርወር ከጀመሩ ወዲሕ የእስራኤል ፖሊስ እድሜያቸዉ ከሐምሳ አመት በታች የሆኑ ፍልስጤማዉያን ወደ ምሥራቃዊ እየሩሳሌም እንዳይገቡ አግዷል

default

የፍልስጤምና የእስራኤል ግጭት

እየሩሳሌም ዉስጥ በፍልስጤም ወጣቶችና በእስራኤል ፖሊስ መካካል የሚደረገዉ ግጭት ሰወስተኛዉን የፍልስጤሞች ኢንቲፋዳ (ሕዝባዊ አመፅ) ይቀሰቅሳል የሚል ሥጋት አሳድሯል። ፍልስጤማዉያን ወጣቶች በእስራኤል ፀጥታ አስከባሪዎች ላይ ድጋይ መወርወር ከጀመሩ ወዲሕ የእስራኤል ፖሊስ እድሜያቸዉ ከሐምሳ አመት በታች የሆኑ ፍልስጤማዉያን ወደ ምሥራቃዊ እየሩሳሌም እንዳይገቡ አግዷል።በተለያዩ የአረብ ሐገሮች የሚኖሩ ፍልስጤማዉያንም ለእየሩሳሌም ወገኖቻቸዉ ድጋፋቸዉን እየገለጡ ነዉ።ግጭቱ የተነሳዉ ዩናይትድ ስቴትስ ፍልስጤምና እስራኤልን ለማስታረቅ አዲስ ጥረት በጀመረችበት ወቅት ነዉ።ዜናነሕ መኮንን ከየሩሳሌም ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።Zenaneh MekonnenNegash Mohamed

Audios and videos on the topic