የፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት ውሳኔ ለሐረሪዎች | ኢትዮጵያ | DW | 27.04.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት ውሳኔ ለሐረሪዎች

ከሐረሪ ክልል ውጭ የሚገኙ የክልሉ ተወላጆች የምርጫ ተሳትፎን በሚመለከት ምርጫ ቦርድ ባሳለፈው ውሳኔ ላይ የቀረበውን ይግባኝ የተመለከተው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት የቦርዱን ውሳኔ ውድቅ ማድረጉን የሐረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ገለፁ፡፡ የሐረሪ ጉባዔ አፈጉባዔ “ውሳኔው ፍትህ የጠገኘበት ነው” ብለዋል፡፡

ውሳኔው ፍትህ የተገኘበት ነው

ከሐረሪ ክልል ውጭ የሚገኙ የክልሉ ተወላጆች የምርጫ ተሳትፎን በሚመለከት ምርጫ ቦርድ ባሳለፈው ውሳኔ ላይ የቀረበውን ይግባኝ የተመለከተው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት የቦርዱን ውሳኔ ውድቅ ማድረጉን የሐረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ገለፁ፡፡ የሐረሪ ጉባዔ አፈጉባዔ “ውሳኔው ፍትህ የተገኘበት ነው” ብለዋል። 
የሐረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ አዩብ አህመድ ለDW በስልክ በሰጡት መግለጫ ከሐረሪ ክልል ውጭ የሚገኙ የክልሉ ተወላጆች የምርጫ ተሳትፎን በሚመለከት ምርጫ ቦርድ ያሳለፈው ውሳኔን በመቃወም የቀረበውን ይግባኝ የተመለከተው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቦርዱን ውሳኔ ውድቅ አድርጓል።
አቶ አዩብ ቀደም ሲልም የምርጫ ቦርድ ውሳኔ የህግ ጥሰት የተፈፀመበት መሆኑን ጠቅሰው ለፍርድ ቤት የቀረበው ይግባኝ ይህንኑ በዝርዝር ያስቀመጠ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የህገ መንግስት ድንጋጌዎች ህገመንግስታዊ ስርዓትን ተከትለው ካልተቀየሩ በስተቀር ህገመንግስቱን እንዲያስፈፅሙ የተቋቋሙ የህገ መንግስት ተቋማት ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ተከትለው መስራታ እንዳለባቸው ፓርላሜንታዊው ስርዓት ያስቀምጣል ያሉት አቶ አዩብ የዛሬው ውሳኔ ይንን መጣስ እንደማይቻል ያረጋገጠ ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይ ቦርዱ ውሳኔውን ተቀብሎ ተግባራዊ ያደርጋል ብለው እንደሚምኑ ተናግረዋል። የሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ አፈ ጉባዔ አቶ ሙህየዲን አህመድ በበኩላቸው ውሳኔው “ፍትህ የተገኘበት ውሳኔ” መሆኑን ለ «DW» በስልክ በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል። የሀረሪ ብሔራዊ ጉባዔ የብሄረሰቡ አባላት የምርጫ ተሳትፎን በሚመለከት ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያሳለፈው ውሳኔ ህገመንግስትን የሚጥስ ነው ሲል ተቃውሞ ማቀረቡ የሚታወስ ነው።

መሳይ ተክሉ 

አዜብ ታደሰ 

ነጋኅ መሐመድ 

Audios and videos on the topic