የፊፋ ባለስልጣናት የጉቦ ቅሌት | ስፖርት | DW | 01.12.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ስፖርት

የፊፋ ባለስልጣናት የጉቦ ቅሌት

ዓለም ዓቀፉ የእግር ኳስ ማህበር ፊፋ አንዳንድ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላቱ በጉቦ ቅሌት ስማቸው አደባባይ ወጥቶ መነጋገሪያ ሆነዋል።

default

ኢሳ ሀያቱ ከፊፋ ፕሬዝዳንት ጋር

ፊፋን አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው የባለስላጣናቱ የጉቦ ቅሌት ነገ በዙሪክ ስዊዘርላንድ በሚካሄደውና የቀጣዮቹ ሁለት የዓለም ዋንጫ ውድድሮችን ለማስናገድ በዕጩነት የቀረቡትን ሀገራት ለመምረጥ በሚከናወነው የድምጽ አሰጣጥ መርሃ ግብር ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚፈጥር ተነግሯል። ፓኖራማ የተሰኘው የእንግሊዙ የዜና ማሰራጪያ ኮርፖሬሽን ቢቢሲ ፕሮግራም፤ በፊት ስማቸው ከጉቦ ጋር ተያይዞ ከተጠቀሱት 3ቱ ባለስልጣናት በተጨማሪ አራተኛውን ከትላንት በስቲያ አጋልጧል። መሳይ መኮንን ዘገባ አለው።

በእርግጥ ፊፋ በቅሌት እየታመሰ ነው። የእንግሊዙ የዜና ማሰራጪያ ኮርፖሬሽን ቢቢስ ፕሮግራም ፓኖራማ እንዳጋለጠው ከ1989 እስከ 1999 እ.ኤ.አ ባሉት ዓመታት ከ24ቱ የፊፋ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሶስቱ በድምሩ 100 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ኪሳቸው ከተዋል። ይህ ገንዘብ በተለያዩ ጊዜያት የተቀበሉት ሲሆን እስከ 2001 እ.ኤ.አ የፊፋ አጋር ሆኖ በቆየው አንድ የቴሌቪዥን ኩባንያ አማካኝነት ነው እጃቸው ያን ያህል ገንዘብ የገባው። የብራዚል ስፖርት ፌዴሬሽን ተወካይ ሪካርዶ ታይክሴራ፤ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኢሳ ሀያቱና የደቡብ አሜሪካው ስፖርት ማህበር ተወካይ ኒኮላስ ሌውዝ ናቸው 100 ሚሊዮን ዶላሩን ለሶስት የተቀራመቱት-እንደ ፓኖራማ ዘገባ። ከዚህ ቀደም ሁለት የስራ አስፈጻሚ አባላት በተመሳሳይ ጉዳይ ከፊፋ ታግደዋል። የዶቸ ቬሌ የስፖርት ፕሮግራም አዘጋጅ ስቴፈን ሄስል አሁን ስማቸው የተነሱት ሶስቱ ባለስልጣናት ላይ የሚወሰድ እርምጃ ይኖራል ብዬ አላስብም ይላል።

ድምጽ

«ሁለቱን ባለስልጣናት በተመለከተ የናይጄሪያው የፊፋ አባል 3 ዓመት፤ ሁለተኛው ሁለት ዓመት ታግደዋል። አሁን የተጠቀሱትን ሶስቱን ግለሰቦች በተመለከተ ፊፋ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጋል። ምናልባት የነገው ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ ከስልጣናቸው ሊያነሳቸው ይችላል። »

መሳይ መኮንን
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic