የፊልም ፕሮዲውሰር እና ዳሬክተር -ቅድስት ባየልኝ | ባህል | DW | 16.01.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የፊልም ፕሮዲውሰር እና ዳሬክተር -ቅድስት ባየልኝ

በቅርብ የወጣውን ፊልሟን ለማስተዋወቅ ከዮናይትድ እስቴትስ ሰሞኑን ወደ ኢትዮጵያ ብቅ ካለችው የፊልም ባለሙያ- ቅድስት ባየልኝ -ጋ የዛሬው የወጣቶች መድረክ ያስተዋውቀናል።

default

ቅድስት ባየልኝ  እስካሁን ሶስት ፊልሞችን ሰርታ ለዕይታ አቅርባለች። አሁንም የመጨረሻ ፊልሟን ለማስተዋወቅ በኢትዮጵያ ትገኛለች። ቅድስት ስለምትሰራቸው ፊልሞች ብቻ ሳይሆን ስለሷ የህይወት ታሪክ መለስ ብላ ታስታውሰናለች።

ቅድስት ባየልኝ  ያጠናችው የስነ ልቦና ትምህርት ነው። ሙያዋ ግን ፤ የፊልም ፕሮዲውሰር እና አዘጋጅ።  አንድ የፊልም አዘጋጅ ስላለበት ኃላፊነት እና ስራ፤  ከፊልም አቀናባሪዎች፣ ከፊልም ቀረፃ ባለሙያዎች እና  ተዋናዮች ጋ ፣ቅስድት ምን አይነት ቅርበት  እንዳላት እንዲሁም ለሌሎችም ጥያቄዎች መልስ ሰታናለች።  

የወጣት ልጆችን ፈተና በተለይም በውጭው አገር ያለውን ፈተና ለማንፀባረቅ ስለጣረችበት -«ከአትላንቲክ ባሻገር» ፊልም ፤ የበለጠ ማወቅ ከፈለጉ ዝርዝሩን ከዛሬው የወጣቶች ክፍለ ጊዜ ያገኙታል።

 ልደት አበበ 

Audios and videos on the topic