የፉኩሺማ አንደኛ አመት መታሰቢያ | ባህል | DW | 16.03.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ባህል

የፉኩሺማ አንደኛ አመት መታሰቢያ

በፉኩሺማ በደረሰው የመሬት ነውፅ እና ሱናሚ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በጃፓን የታየው የተፈጥሮ አደጋ አለም አቀፉን ህብረተሰብ፣ አሳዝኗል፣ መለስ ብሎም እንዲያስብ አድርጓል።

A woman wearing a mask looks at paper lanterns created at a memorial for the victims of the March 11 earthquake and tsunami in Koriyama, Fukushima prefecture March 10, 2012, a day before the one-year anniversary of the disaster. The magnitude 9.0 earthquake on March 11, 2011 unleashed a tsunami that killed about 16,000 and triggered the world's worst nuclear crisis since Chernobyl. REUTERS/Yuriko Nakao (JAPAN - Tags: DISASTER ANNIVERSARY TPX IMAGES OF THE DAY) /sc

የፉኩሺማ አንደኛ አመት መታሰቢያ

በፉኩሺማ በደረሰው የመሬት ነውፅ እና ሱናሚ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት አልፏል።  በጃፓን የታየው የተፈጥሮ አደጋ አለም አቀፉን ህብረተሰብ፣ አሳዝኗል፣ መለስ ብሎም እንዲያስብ አድርጓል።

ጃፓን ከአንድ ዓመት በፊት በመሬት ነውፅና ማዕበል ሳቢያ የሞቱትንና የደረሱበት ሳይታወቅ የጠፉትን ከ 19 ሺህ የሚበልጡ የተፈጥሮ ቁጣ ሰለባዎች ባለፈው ሳምንት አስባለች። ዕለቱን ምክንያት በማድረግ በቶኪዮና በሌሎች ከተሞች በአደባባይ የተሰለፉ የሐገሪቱ ዜጎች የአቶም ሃይል ጣቢያዎች በሙሉ እንዲዘጉ ጠይቀዋል። እዚህ ጀርመንም የጃፓኑን መታሰቢያ ዕለት ምክንያት በማድረግ በርካታ የተፈጥሮ ተንከባካቢዎች ጸር-ኑክሌያር ተቃውሞ አሰምተዋል።  የበርሊን ከተማ ነዋሪ የሆነው -ፓትሪክ፤ የፉኩሺማን አስከፊ አደጋ እንደ በርካታ ጀርመናዊያን በመገናኛ ብዙኃን ተከታትሏል። ይሁንና ዘገባው ለሱ በቂ አልነበረም። « ማለት አሁን 2ኛ እና 3ኛው  የፉኩሺማ የአቶም ሃይል ጣቢያዎች በጠቅላላው የፍንዳታ ድምፅ እንዳሰሙ አውቃለሁ። ግን ይህ በዜና አልቀረበም። ምክንያቱም የአውሮፓ ትኩረት ሌላ ነገር ላይ ነበረና!»

Hand out photo of Unit 3 of Fukushima Daiichi Nuclear Power Station pictured from a helicopter on March 16, 2011, Okumamachi, Japan. Plutonium has been found in soil at various points within Japan's stricken Fukushima Daiichi nuclear complex but does not present a risk to human health, operator Tokyo Electric Power Co (TEPCO) said on Monday. Skip related content TEPCO vice-president Sakae Muto told journalists at the company's latest briefing that test results showing the plutonium came from samples taken a week ago. It was the latest bad news from the plant, where evidence of radiation has been mounting and engineers face a protracted battle to control reactors damaged by an earthquake and tsunami on March 11. Photo via ABACAPRESS.COM

የአቶም ሃይል ጣቢያ -ፉኩሺማ

በርግጥ አውሮፓን በአሁኑ ሰዓት የሚያሳስባት እንደ ግሪክ የፋይናንስ ቀውስ የመሳሰሉ ጉዳዮች አሉ። ይሁንና የፉኩሽማ አደጋ ትልቅ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኖ ሰንብቷል። የጃፓን አሳዛኝ ጥፋት ጀርመን ነገ በኔ ነው ብላ ርዕሷ አደረገች፤ ምክንያቱም እንደ ጃፓን ጀርመንም የኤሌክትሪክ ኃይል የምታመነጭበት በርካታ የአቶም ጣቢያዎች  አሏት።

ይህም ጉዳይ ለብዙ አመታት ርዕስ ሆኖ ሁሉም ፖለቲከኞች ሲወያዩበት ቆይተዋል። ካርል ቤር -ከአረንጓዴዎቹ ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ነው።

« በርግጥ ብዙ በጎ ነው ብዬ ስለፉኩሺማ መናገር አልችልም ግን ከዚህ አንድ ልንማር የምንችለው ነገር ካለ፤ የኒኩሌር የሀይል ምንጭ ያህል አደገኛ እንደሆነ እና በአገልግሎት ላይ መዋል እንደሌለበት ነው።»

Demonstranten mit Plakaten und Fahnen stehen am Sonntag (11.03.2012) bei einer Kundgebung auf einer Anti-Atomkraft Demonstration vor dem AKW Brokdorf. Ein Jahr nach der verheerenden Atomkatastrophe im japanischen Kernkraftwerk von Fukushima demonstrierten vor dem AKW Brokdorf, laut Veranstalter, rund 3000 Demonstranten gegen Atomkraft. Foto: Malte Christians dpa/lno

ጸረ-ኑክሌያር ተቃውሞ በጀርመን

የጀርመን መንግስት እኢአ በ2000 ዓ ም እስከ ከ2022 ድረስ በአጠቃላይ የአቶም ሃይል ጣቢያዎቹን እንደሚዘጋ አሳውቋል። በርግጥ ጀርመን በ2022 የአቶም ኃይል ታቆም ይሆን?  ፍሬአ ቴን በበርሊን አደባባይ ወተው ጸር-ኑክሌያር ተቃውሞ ካሰሙት ውስጥ አንዷ ነች።

« ከትምህርት ቤቴ እና የክፍሌ ልጆች፤ ከዚህ ቀደም ጨርሶ በፖለቲካ ውስጥ የሌሉበት ወይንም የተለያየ የፖለቲካ አቋም የነበራቸው በሙሉ ተሰብስበን አንድ ነጥብ ላይ ሁላችንም ተስማምተን አንድ የሆነ ስሜት ፈጠርን። »

ከፉኩሺማ አደጋ በኋላ ጀርመን ሰባት ያረጁ የአቶም ሃይል ጣቢያዎቿ ተዘግተው እንዲቆዩ ወስናለች። የበለጠ የፉኩሺማ አንደኛ አመት መታሰቢያን በተመለከተ የቶኪዮ ዘጋቢያችን ወሰንሰገድ መርሻ ያጫወተን አለ። ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

 ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 16.03.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14L9Q
 • ቀን 16.03.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14L9Q