የፈጠራ ስራ ባለቤት- ቴዎድሮስ ንጉሴ | ባህል | DW | 22.11.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የፈጠራ ስራ ባለቤት- ቴዎድሮስ ንጉሴ

ቴዎድሮስ ንጉሴ የጫማ ቅርፅ ያለው የሊስትሮ ኪዮስክ በመስራት የፈጠራ ስራ ባለቤት ነው። ይህ ዓይነት ሀሳብ እንዴት እንደመጣለትና በተግባር እንደተረጎመው ይገልፅልናል።

Äthiopien, Schuhputzer, Kongress , Kongreß, Listros, Hamburg, Ausstellung

ቴዎድሮስ ንጉሴ በአሁኑ ሰዓት በፅዳት ሥራ ተሰማርቶ ይገኛል። ወጣቱ ይህንን ሙያ የተማረው በዓረብ ሀገር ቆይታው ሲሆን ወደ ሀገሩ ተመልሶም በዚሁ ሙያ ገፍቶበታል። ይህ ብቻ አይደለም፤ ቴዎድሮስ ከስራው ጎን ሌላ አንድ ሀሳብም ነበረው። ይህንንም ሀሳብ ዕውን አድርጎ አዲስ ነገር እስከመፍጠር ድረስ ገፍቶበታል። ይህም የጫማ ቅርፅ ያለው የሊስትሮ ኪዮስክን ነድፎ መገንባት ነበር። ለዚህም ያነሳሳው በአዲስ አበባ የሊስትሮ ሰራተኞች ሁኔታ ስላሳሰበው እንደሆነ ይናገራል።

ቴድሮስ የ 12ኛ ትምህርቱ አጠናቋል። በሊስትሮነት ሙያ አላለፈም። ታድያ የፈጠራህ ስራው እንዴት በሊስትሮ ሥራ ላይ አተኮረ? ሀሳቡን ከየት አመነጨው? ገልፆልናል። ቴዎድሮስ ከአንድ ዓመት በፊት የፈጠራ ስራው እውቅና አግኝቶ የባለቤትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እንዲያገኝ የሄደው ወደ አምዕሮኦዊ ንብረት ነበር። እዛም ማሟላት ስለነበረበት መስፈርት አጫውቶናል። ሁሉንም ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic