የፈረንሳይ ፖሊስ የካሌ ስደተኞች በደል | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 31.10.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የፈረንሳይ ፖሊስ የካሌ ስደተኞች በደል

የፈረንሳይ ፖሊስ በካሌ ስደተኞች ህጻን አዋቂ ሳይለይ ጥቃት እና በደል ፈጽሟል በሚል በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ለሚቀርብበት ተደጋጋሚ ክስና ወቀሳ መንግሥት ለመጀመሪያ ጊዜ መልስ ሰጠ። የፈረንሣይ ፖሊስ የካሌ ስደተኞች ላይ ጥቃት እና በደል በመፈጸም ስደተኞች ላይ የሚረጭ አቃጣይ ንጥረ-ነገርም ይጠቀማል የሚል ነው ክሱ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:25
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:25 ደቂቃ

የፈረንሳይ ፖሊስ የካሌ ስደተኞች በደልን በተመለከተ መልስ ሰጠ

የፈረንሳይ ፖሊስ በካሌ ስደተኞች ህጻን አዋቂ ሳይለይ ጥቃት እና በደል ፈጽሟል በሚል በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ለሚቀርብበት ተደጋጋሚ ክስና ወቀሳ መንግሥት ለመጀመሪያ ጊዜ መልስ ሰጠ። ወደ እንግሊዝ ለመሻገር በፈረንሣይ ግዛት በምትገኘው ካሌ ጫካ ውስጥ በጎስቋላ ድንኳኖች ተጠልለው በነበሩት ላይ የፈረንሣይ ፖሊስ በፈጸመዉ ጥቃት እና በደል የሚረጭ አቃጣይ ንጥረ-ነገርም ይጠቀማል የሚል ነው ክሱ። 

የፈረንሣይ መንግሥት በሀገር ውስጥ ሚንሥትርሩ በኩል በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የቀረበበትን ክስ እና ውንጀላዎች በጽሑፍ መግለጫ አስተባብሏል። «ተጨባጭ መረጃ እንኳን ባይገኝም የኃይል አጠቃቀም እና ሕግን መተላለፍ እንዲሁም የሥነ-ምግባር ጥሰት የመኖሩን ትክክለኛነት» ማረጋገጡን ግን በዘገባው ላይ አመልክቷል። የፈረንሣይ ፖሊስ በስደተኞች ላይ በሚፈጽመው ተገቢ ያልሆነ የኃይል ጥቃት በተደጋጋሚ ክሶችን የሚያቀርበው (Human Right watch) እና ሌሎች የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በትክክልም ችግሩ መኖሩን በመጥቀስ የፈረንሣይ መንግሥት በዚሁ ጉዳይ ላይ «ምላሽ መስጠቱ አንድ ርምጃ ቢሆንም ያለአግባብ በስደተኞች ላይ ኃይል በሚጠቀሙ ፖሊሶች ላይ ተጠያቂ የሚያደርግ አሠራር  መዘርጋት አለበት» ብለዋል። 

ሐይማኖት ጥሩነህ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ
 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች