የፈረንሳይ ምርጫ እና አፍሪቃውያን  | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 28.04.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የፈረንሳይ ምርጫ እና አፍሪቃውያን 

ለፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ምርጫ ለሁለተኛ ዙር የደረሱት እጩዎች አፍሪቃ እና የቅኝ ግዛት ላይ ያላቸው አተያይ እጅጉን ተቃራኒ ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:10

የፈረንሳይ ምርጫ እና አፍሪቃውያን 

ቀኝ አክራሪዋ ለ ፔን የቅኝ ግዛት አዎንታዊ ትሩፋቶች በፈረንሳይ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ሊካተት ይገባል ባይ ናቸው። ባለፈው ታኅሳስ ወደ አልጄሪያ ተጉዘው የነበሩት የቀድሞው የኤኮኖሚ ሚኒሥትር ኤማኑዌል ማክሮ በበኩላቸው ፈረንሳይ ሰሜናዊ አፍሪቃን ቅኝ መግዛቷ «በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል ነው» ሲሉ የሰጡት አስተያየት ብዙ አስተችቷቸዋል።ማክሮ ትችት ሲያይልባቸዉ፤ በአልጄሪያ ጉብኝታቸው ወቅት በቴሌቭዥን ፊት ቀርበው «ወንጀል የፈጸምንባቸውን ዜጎች ይቅርታ ልንጠይቅ ይገባል» ሲሉ የሰጡትን አስተያየት  አጥፈውታል። ማክሮ የኋላ ኋላ ቅኝ አገዛዝ «የሥልጣኔ እና ጭካኔ ድርጊቶች ቅይጥ ነው» ወደ ሚል የተበረዘ ብያኔ ተመልሰዋል። በሰሜን አፍሪቃ አገራት ፖለቲካ እና ኤኮኖሚ ከፍ ያለ ሚና ያላት ፈረንሳይ የምታደርገዉ ምርጫ ለቀድሞዎቹ የቅኝ ግዛት አገሮች የሚኖረው ትርጓሜ ምን ይሆን?

 ይልማ ኃይለሚካኤል

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ 
 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች