የፈረንሳይና ጣሊያን ዉዝግብ በሼንጌን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 27.04.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የፈረንሳይና ጣሊያን ዉዝግብ በሼንጌን

አራተኛው የዜና መጽሄት ርዕሳችንም ትኩረቱ በጣልያንና ፈረንሳይ ላይ ነው። የሼንጌን ቪዛ የያዘ ሰው፤ በሼንጌኑ ውል መሰረት በአባል ሀገራት ያለቪዛ መንቀሳቀስ ይችላል። ሰሞኑን ግን ጣሊያን ቪዛ ሰጥታ ወደ ፈረንሳይ የሰደደቻቸውን ስደተኞች ፈረንሳይ ከድንበር ላይ አቁማ በመጡበት እግራቸው መልሳቸዋለች።

የፈረንሳይና የጣሊያን መሪዎችለውይይት

የፈረንሳይና የጣሊያን መሪዎች ለውይይት

ሁኔታው በፈረንሳይና ጣሊያን መካከል እሰጥ-አገባ ፈጥሮ ቆይቷል። የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በጉዳዩ ላይ ተገናኝተው ቢወያዩም ለጊዜው ግን ከስምምነት ላይ አልደረሰሱም። ለመሆኑ የሼንጌን ስምምነት ምንድን ነው? ዓላማውስ ምን ይመስላል? ተክሌ የኌላ የብራስልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሴን ከጥቂት ሠዓታት በፊት አነጋግሮት ነበር። ገበያው የሼንጌን ውል ታሪካዊ ዳራን ባጭሩ በማስቀመጥ ይጀምራል።

ገበያው ንጉሴን

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ተክሌ የኋላ