የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያን ጅቡቲን እና ኬንያን ይጎበኛሉ  | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 08.03.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያን ጅቡቲን እና ኬንያን ይጎበኛሉ 

ከሰኞ እስከ አርብ የሚዘልቀው ጉብኝታቸው ዓላማ የፈረንሳይን እና የሀገራቱን ኤኮኖሚያዊ ፣ ወታደራዊ የንግድ እና የባህል ትብብር ይበልጥ ማጠናከር መሆኑን የፈረንሳይ መንግሥት አስታውቋል። ፕሬዝዳንት ማክሮ በኢትዮጵያ በሚያደርጉት የሁለት ቀናት ጉብኝት ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነቶች ላይ ይወያያሉ ተብሏል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:26

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት የምሥራቅ አፍሪቃ ጉብኝት

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑዌል ማክሮ በሚቀጥለው ሳምንት ኢትዮጵያን ጅቡቲን እና ኬንያን ይጎበኛሉ። ከሰኞ እስከ አርብ የሚዘልቀው ጉብኝታቸው ዓላማ የፈረንሳይን እና የሀገራቱን ኤኮኖሚያዊ ፣ ወታደራዊ የንግድ እና የባህል ትብብር ይበልጥ ማጠናከር መሆኑን የፈረንሳይ መንግሥት አስታውቋል። ፕሬዝዳንት ማክሮ በኢትዮጵያ በሚያደርጉት የሁለት ቀናት ጉብኝት ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነቶች ላይ ይወያያሉ ተብሏል። ከሚያተኩሩባቸው ጉዳዮች ውስጥም ወታደራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ትብብር እንደሚገኙበት ተገልጿል። ማክሮ በኢትዮጵያ ቆይታቸው የላሊበላ ውቅር ዐብያተ ክርስቲያንን ይጎበኛሉ፤ ከአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ጋርም ይነጋገራሉ። የፓሪስዋ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ ዝርዝሩን አዘጋጅታለች። 
ሃይማኖት ጥሩነህ
ሩት መለሰ
ተስፋለም ወልደየስ

Audios and videos on the topic