የፀጥታ ሁኔታ በኢትዮጵያ  | ኢትዮጵያ | DW | 11.01.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የፀጥታ ሁኔታ በኢትዮጵያ 

የኢትዮጵያ የፀጥታ ምክር ቤት ሊቀመንበርና የመከላክያ ሚንስትር አቶ ስራጅ ፈጌሳ በሃገሪቱ ዉስጥ ያለዉን የፀጥታ ሁኔታ በተመለከተ ትላንት ለጋዜጠኞች ማብራርያ ሰተዋል። ሚኒስትሩ በዩኒቨርስቲዎች ዉስጥ በታየዉ አለመረጋጋት ላይ የተሳተፉትን ግለሰቦች ማንነት እያጣሩ እንደሚገኙና ሌሎች ላይ ደግሞ ርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:45

የኢትዮጵያ ፀጥታ ሁኔታ

የኢትዮጵያ የፀጥታ ምክርቤት ሊቀመንበርና የመከላክያ ሚኒስትር አቶ ስራጅ ፈጌሳ በትላንትናዉ እለት በሃገሪቱ ዉስጥ ስላለዉ የፀጥታ ጉዳይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል። ሚኒስትሩ በመግለጫቸዉ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ከተነሳ በኋላ «በዋነኛነት ሁሉም አከባቢ በሚባል ደረጃ የተሻለ መረጋጋት» እንደነበረና «ቀስ በቀስ በነበሩት ሂደቶች አንድ አንድ አካባቢዎች ላይ ተመሳሳይ ሁከቶች፣ አለመረጋጋትና ወደ ግጭቶች የሚሻጋገሩ ሁኔታዎች» መከሰቱን ተናግረዋል።

በኦሮሚያ፣ በአማራና በትግራይ ክልሎች እንዲሁም ድሬዳዋ ዉስጥ ባሉት የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዉስጥ ግጭቶች መከሰታቸዉንም አቶ ስራጅ ፈጌሳ ተናግረዋል። በዚህ የትምህርት ተቋም ዉስጥ «በዘረኝነት የተዘፈቁ» ያሏቸዉንና በወንጀል የተሳተፉትን በሕግ እንዲጠየቁ መደረጋቸዉን ተናግረዋል። እስከ 19 ዩኒቨርስቲዎች በዚህ አለመረጋጋት መጎዳታቸዉን የተናገሩት የመከላክያ ሚኒስትሩ ላለፉት ዓመታት «በዲሲፕሊን እና በአካዴሚክ» ግድፈት ከተቋሙ የተሰናበቱት ከጊቢዉ ሳይወጡ የተከሰቱትን ግጭቶች ስያባብሱ የነበሩም አሉ ሲሉ ገልፀዋል።

የአምቦ ዩኒቨርስቲ መምሕርና የበየነ መረብ «ኢንተርኔት» ፀሐፊ ስዩም ተሾመ ከዩኒቨርሲቲ ተሰናብተዉ ግን እዛዉ በዩንቨርስቲ ዉስጥ የሚቀመጡ ካሉ የማጣራቱን ርምጃ መዉሰድ ያለበት ዩኒቨርስትዎቹ ወይም የትምህርት ሚንስቴር ነዉ ይላሉ። የፀጥታ ምክርቤት ወይም የመከላክያ ሚኒንስቴሩ በዚህ ዉስጥ ጣልቃ  መግባቱ «ፍፁም አምባገነንነት» ነዉ ሲሉ ስዮም አክሎበታል።

የሃገሪቱ ፀጥታ አካል ወደ ኦሮሚያና ኢትዮ ሶማሌ ክልሎች ባይላኩ ኑሮ «እጅግ ዘግናኝ የሆነ እልቂት ይከሰት» ነበር ሲሉ አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ ተናግረዋል። በኦሮምያ ክልል በምስራቅ ሃረርጌ ዞን በጨለንቆ የመከለክያ ሠራዊት አባሎች መገኘታቸዉ ከክልሉ እዉቅና ዉጭ እንደሆናና ለፈፀሙት ግድያም ተጠያቂ  እንደሆኑ ተዘግቦ ነበር። ይህን ጉዳይ በተመለከተ የመከላከያ ሚኒስትር ስራጅ ፈርጌሳ ለገዥጠኞች ይህን መልስ ሰተዋል።

የፀጥታ ምክርቤት ሊቀመንበርና የመከላክያ ሚኒስትር አቶ ስራጅ ፈጌሳ በሃገሪቱ ዉስጥ የተፈጠረዉን አለመረጋጋትን ለማባባስ ሕገ-ወጥ መሣርያ ወደ ሃገሪቱ መግባቱን በመግለጫቸዉ ተናግረዋል። በዚህም  መሰረት 270 ክላሽንኮቭ፣ 200 ሽጉጥ፣ 65 ሺህ የክላሽ ጥይትና፤ አንድ ሺህ የመትረየስ ጥይት በቁጥጥር ስር መዋሉንም አክለዉ ገልፀዋል።

 
መርጋ ዮናስ 
አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ        

Audios and videos on the topic