የፀረ አፓርታይድ ታጋይ ዊኒ ማንዴላ የትግል ሕይወት | አፍሪቃ | DW | 03.04.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የፀረ አፓርታይድ ታጋይ ዊኒ ማንዴላ የትግል ሕይወት

ዕውቋ የደቡብ አፍሪካ የፀረ አፓርታይድ ታጋይ እና የቀድሞው የኔልሰን ማንዴላ ባለቤት ዊኒ ማድኬዜላ ማንዴላ ትላንት በ81 ዓመታቸው አርፈዋል፡፡ ከባለፈው ጥር ወር ጀምሮ በህመም ሆስፒታል ሲመላለሱ የቆዩት ዊኒ ትላንት ህይወታቸው ያለፈው ህክምና እየተከታተሉበት በሚገኘው ሆስፒታል በቤተሰባቸው እንደተከበቡ እንደነበር ተዘግቧል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:47

የዊኒ አድናቂዎች «የደቡብ አፍሪካ እናት» ይሏቸዋል

ዊኒ ማድኬዜላ ማንዴላ የነጮች የበላይነትን የሚያቀነቅነውን የአፓርታይድ ስርዓትን በመቃወም በተደጋጋሚ ለእስራት ተዳርገዋል፡፡ የኔልሰን ማንዴላ የመጀመሪያ ሚስት የነበሩት ዊኒ ባለቤታቸው በሮቢን ደሴት ለ27 ዓመታት በታሰሩበት ወቅት ከእስር እንዲለቀቁ በደቡብ አፍሪካም ሆነ ከሀገራቸው ውጭ በርካታ ዘመቻዎች አካሄደዋል፡፡ ዊኒ ዘረኝነት እንዲጠፋ ጠንካራ ታጋይ፣ በደቡብ አፍሪካ ዲሞክራሲ እንዲሰፍንም ኃይለኛ ተሟ ጋች እንደነበሩ ብዙዎች ይመሰክሩላቸዋል።   

ዊኒ ከቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ ጋር ከመፋታታቸው በፊት ለ38 ዓመታት በትዳር የቆዩ ሲሆን ሁለት ልጆችንም በጋራ አፍርተዋል፡፡ የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል የዊኒ ማንዴላን ህይወት መለስ ብሎ ቃኝቶታል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ። 

ይልማ ኃይለ ሚካኤል 

ተስፋለም ወልደየስ

አርያም ተክሌ 

 

Audios and videos on the topic